በሱፍቃድ ሪል እስቴት ታዋቂዋ ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።https://1234…

Reading Time: < 1 minute
በሱፍቃድ ሪል እስቴት ታዋቂዋ ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።

በ23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ አንድ ሺህ የመኖሪያ ቤትን በ5 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን ለቀጣይ ሁለት አመት የኩባንያውን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።



ከተመሰረተ ገና የሁለት ዓመታት ዕድሜ ያለውና በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት የቤት ፈላጊዎችን ምርጫ ያሟላና ዘመናዊ መንደር እየፈጠረ ይገኛል።

ከዋና ዋና ከተሞች ወጣ ብሎ ወረዳዎችንና አዳጊ ከተሞችን በማነቃቃት፣ የኢንዱስትሪ ልማት ፍሰቶቻቸውን የሚያግዝ፣ የማኅበረሰቡን አኗኗር በማዘመን የከተማ ልማት እያፋጠኑ ከሚገኙ ጥቂት ፕሮጀክቶች ቀዳሚ ነው።

ይህ በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው አዲስ የመኖሪያ መንደር ለቤት ደንበኞቹ አስተማማኝ የቤት ግንባታ አገልግሎት እና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ አሳታፊ የከተማ ልማት ፍልስፍና ይከተላል።

የበሱፍቃድ ሪል እስቴት ልማት ኩባንያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንጃር ሸንኮራዋ አረርቲ ከተማ ስትጠራ ስሙ አብሮ የሚነሳው በሱፍቃድ ሪል ስቴት በ230,000 ካሬ ሜትር ላይ እየተገነባ ያለው ግዙፍ የመኖሪያ መንደር 1,000 ቤቶችን፣ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል፣ ከአጸደ-ሕጻናት እስከ ኮሌጅ ድረስ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ተቋም እና የጤና ተቋማት፣ ለስምጥ ሸለቆዋ የቱሪስት መዳረሻ አረርቲ ተስማሚ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ አዲስ መንደር ነው።

በሱፍቃድ ሪል እስቴት በአጭር ጊዜ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የቤት ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን፣ ከሰሜን አሜሪካና ካናዳ፣ እስራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ኡጋንዳ እና ቻይና አገራት የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ በስፋት የቤት ደነበኞቹ የሚገኙባቸው አገራት ናቸው። ይህ አለም-አቀፍ ተደራሽነቱን እያሰፋ በመሄድ ሌሎች አገራትንም የመድረስ ስትራቴጂ ነድፎ እየሰራ ሲሆን የዛሬው የብራንድ አምባሳደር ሹመትም የዚሁ አካል ነው።

ይህ አዳጊ የሆነችውን አረርቲ ከተማ ከአዳማ፣ ደብረዘይት፣ ሞጆ፣ ደብረብርሃን እና አዲስ አበባ ጋር በልማት፣ የቱሪስት መዳረሻ እና በኮንፍረንስ ቱሪዝም የማስተሳሰር ዐቅም እየፈጠረ የሚገኘው የቤት ልማት ኢንቨስትመንት ብራንዱን ይበልጥ ለማሳደግና በቀጣይ ዓለም-አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ነው ዛሬ ቅዳሜ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ዓመታት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን ሾሟል።
163100cookie-checkበሱፍቃድ ሪል እስቴት ታዋቂዋ ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።https://1234…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE