ናሽናል ፋይናንስ አካዳሚ በኢንሹራንስ ስልጠና ለመስጠት እውቅና ማግኘቱን አስታወቀተቋሙ ከአዲስ አበባ የትምህ…

Reading Time: < 1 minute
ናሽናል ፋይናንስ አካዳሚ በኢንሹራንስ ስልጠና ለመስጠት እውቅና ማግኘቱን አስታወቀ

ተቋሙ ከአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በዲፕሎማ መርሀግብር በኢንሹራንስ ስልጠና ለመስጠት እውቅናና ፍቃድ ተሰቶታል።



ናሽናል ፋይናንስ አካዳሚ በኢትዮጵያን የፋይናንስ ሴክተር የሰው ሀይል ክፍተት በአግባቡ በተረዱ ግለሰቦች አነሳሽነት የተጀመረ የስልጠና ተቋም ነው።

የፋይናንስ ተቋማት በየጊዜው እየተለዋወጠ ከሚገኘው የደንበኞች ፍላጎት ጋር መላመድ የሚቻለው በሰለጠነና ብቁ ሰራተኞችን እኛ መሪወችን በማፍራት ነው ተብሏል።



በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት ውስጥ የፋይናንሱን ሴክተር ፍላጎትና ክፍተት ለመሙላት ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ተቋም ባለመኖሩ ምክንያት ነው ይህንን የስልጠና ማዕከል ለመክፈት ምክንያት የሆነን ብለዋል።

ተቋሙ ፍቃድ ማግኘቱን አስታውቆ በሶስት መርሀ ግብር ስልጠናውን ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።



ስልጠናው ለመውስድ የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞቻቸው ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ተገልጿል።

ስልጠናው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ተግዳሮቶችን በጥልቀት በተረዱ ባለሙያዎች ከ75 በላይ የተግባር ተኮር ክህሎትን መሰረት ያደረጉ ስልጠና እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው።

166760cookie-checkናሽናል ፋይናንስ አካዳሚ በኢንሹራንስ ስልጠና ለመስጠት እውቅና ማግኘቱን አስታወቀተቋሙ ከአዲስ አበባ የትምህ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE