የሮቦት እና የኤ አይ ፈጠራ ውድድር ምዝገባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በተባበሩት መንግስታት አዘጋጅነት በየሁለት ዓመቱ የሚዘጋጀው የሮቦት እና የኤ አይ ፈጠራ ሀገር አቀፍ ውድድሩን ለመጀመር የምዝገባ ሂደቱ በዛሬው ዕለት መከናወን መጀመሩን የ ኤ አይ ፎር ጉድ ፕሮጀክት ማኔጀር ሄለን አቢ ገልጸዋል፡፡

ኤ አይ ፎር ጉድ ፕሮጀክት፤በአርቴፍሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ የፈጠራ ስራዎች እንዲበረታቱ እና የኢትዮጲያ ልጆች በሮቦት ፈጠራ ላይ ያላቸው ግንዛቤ እንዲዳብር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡
በዚህም ከ 10 እስከ 13 በጁኒየር እንዲሁም ከ 14-18 በሲንየር ምድብ፤በተናጥል አልያም በቡድን መወዳደር የሚፈልጉ ከስምንት ባልበለጠ ቁጥር መሪያቸውን በመምረጥ መወዳደር የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱንም አስረድተዋል፡፡

በኤ አይ እና የሮቦት ስራዎች ላይ ዝንባሌው እና ፍላጎቱ ያላቸው ልጆች በኤ አይ ፎር ጉድ ዌብሳይት እየገቡ መመዝገብ እንደሚችሉ የገለጹት ፕሮጀክት ማኔጀሯ በዚሁ ውድድር ላይም እስከ 5ሺህ የሚሆኑ ልጆች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡
ወደ 40 የሚሆኑ የአፍሪካ እና የአለም በሚሳተፉበት መድረክ ላይ ኢትዮጲያም አንደኛዋ ሆና በዘርፉ አሸናፊ ለመሆን አዲስ አበባን ጨምሮ ከክልል ከተሞች የሚመጡ ልጆችን በማሰልጠን ለውድድር ብቁ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡
ሀገር አቀፍ ውድድሩ እ.ኤ.አ ማርች 15 በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዘየም እንደሚካሄድ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ አለም አቀፍ ውድድደሩ ደግሞ ከጁላይ 8-12 ሲውዘርላንድ ጄኔቫ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡

ማንኛውም በዚህ ውድድር ላይ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የመመዝገቢያም ሆነ የስልጠናና እና ሌሎች ልምምዶችን ካለ ምንም ጠአገልግሎት ክፍያ በነጻ ማግኘት እንደሚችሉም ጭምር ነው፤የ ኤ አይ ፎር ጉድ ፕሮጀክት ማኔጀር ሄለን አቢ የገለጹት፡፡