24 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለቆጣቢዎች

Reading Time: 2 minutes
ያብራክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኀብረት ስራ ማኅበር አማካኝነት ለቆጠቡ መኪና ፈላጊዎች በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ በተከናወነ ልዩ መርሐግብር 24 የሚደርሱ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን አስረከበ።

የያብራክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኀብረት ስራ ማኅበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያለምተስፋ ተሾመ እንደገለፁት በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥን እያሳየ የሚገኘው ያብራክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኀብረት ስራ ማኅበር ዜጎች ህይወታቸው እንዲለወጥ ጠንክሮ በመስራት ላይ ሲሆን በማኀበራዊ ተሳትፎ በኩል በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችን በአነስተኛ የብድር ወለድ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ የመንግስትና የግል ተቋም ሰራተኞች እንዲሁም በተለያየ የግል የስራ ዘርፍ ተሰማርተው ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በሁለት ዙር ከ54 በላይ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ መኪኖችን በደማቅ ሁኔታ ማስረከብን አቶ ያለምተስፋ ተሾመ ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ መኪናዎን እያቀረበ የሚገኘው ጎሸር ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ መኮነን እንደገለጹት “መኪኖዎቻችን በኤሌክትሪክ ቻርጅ መሥራታቸው ለሀገር ብዙ ጥቅምን ያስገኛሉ ያሉ ሲሆን አሁን ላይ አለም የደረሰበት የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸውን ተሽከርካሪዎችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ” ገልጸዋል።

 
162970cookie-check24 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለቆጣቢዎች

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE