“ጃን ሜዳ” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ዘ-ኢ ትዮጵያ የተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት የተመሠረተበትን አምስተኛ አስመልክቶ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የጃን ሜዳ ፕሮጀክት የተለያየ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ባለሙያዎች በተገኙበት አስተዋውቃል።
የሥራ ዕድል ፈጥሮ ለማሰማራት፣ ማዕድ ለመመገብ፣ጸጉር ለማስተካከል፣ገላ ለማጠብ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ መዝናኛ እድል ፈጥሮ ሁሉንም ችግረኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።
ታህሳስ 2012 ዓ.ም የተመሠረተው ዘ-ኢ ትዮጵያ የተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት በዋናነት የሚሠራው በየጎዳናው የወደቁ ወገኖቹን ዘር፣ቀለም፣ጾታ፣ሃይማኖት ወ.ዘ.ተ ሳይለይ ለሁም የሰው ዘር ሁሉ በእኩልነት በመርዳት የሚሠራ ሀገር በቀል ተቋም ሲሆን ባለፉት አምስት አመታት በቁጥር በጣም በርካታ ወጎኖችን የሥራ እድል በመፍጠር፤ እንዲሁም ወጣቱን በማነቃቃትና ከአላስፈላጊ ሕይወት በማውጣት የቤት ኪራይ መክፈል፣አልባሳት በማልበስ፣ በሁለት ሳምንት አንዴ አስቪዛ በመስፈር፣ ፍራሽ ልብስ ጫማ የቤት ዕቃ በማሟላት ለአካል ጉዳተኞች ዊልቸር ለዓይነ ስውራን አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁስ በመስጠት ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎችን በማስተማርና በማስመረቅም ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ጊዜ 86 አባ ዎራዎችን እና 300 ቤተሰቦችን በቋሚነት እየረዳም የሚገኘው ማኀበር በጣና ገዳማትም ለሁለት ዓመታት የእንቦጭ ለቀማ ሲያካሂድ የነበረ እና ጥንታዊ ቅርስ የሀገር ሀብት የሆኑ ቦታዎችን ከመንከባከብ አንጻር በጣና ገዳማት ላይ የወደብ መጸዳጃ ቤት ሠርቷል።