የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል 2024
በአፍሪካ የመጀመሪያው የብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል ማስጀመሪያ የሆነው የኢትዮ ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል በመጪው ታህሣሥ ወር በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
ፌስቲቫሉን የጎፍ ኢንተርቴይመንት ከኢፌዴሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ከኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ጋር ጥምረት ፈጥረው ያሰናዱት ሲሆን መርሐግብር ከፊታችን ከታህሣሥ 11 እስከ ታህሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ አራት የሚቆይ ሲሆን መርሐግብሩ የብሪክስ ሀገራት የፊልምና የቴሌቪዥን ፌስቲቫል ማስጀመሪያ መሆኑን አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።
የፌስቲቫሉም ዓላማ በቻይና እና ኢትዮጵያ ለሚገኙ የፊልም ትምህርት ተቋማት የፊልም እውቀት ሽግግር ማምጣት እንዲሁም ከሀገራችን ኢትዮጵያ በተሻገረ መልኩ በአህጉራችን አፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ መነቃቃት እንዲፈጠር ድልድይ ሆኖ ማገናኘት መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በማዕድን ፣ በኮንስትራክሽን እንዲሁም በአምራች ዘርፎች በርካታ ስራዎችን በጋራ የሚሰሩና ረጅም ዓመታት የተሻገረ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ዘርፎች በተጨማሪም በፊልሙም ዘርፍ የራሳቸውን የእውቀት እና ልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደ ኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን ይህም ፌስቲቫል የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ጋር ቀጣይነት ያለው ትብብር እና የባህል ትስስርን በማጠናከር ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልጿል።
የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሥነ-ጥበብና ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በመግለጫው እንደገለጹት ፌስቲቫሉ ረጅም ዓመታት ልምድና እውቀት ካላቸው የቻይና የፊልም ባለሞያዎች በርካታ ተሞክሮዎችን የኢትዮጵያ የፊልም ዘርፍ የሚያገኙበት እንዲሁም ኢትዮጵያ ያላትን የፈጠራ ኢንዱስትሪዎቿን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የባህል አማካሪ ዣንግ ያዋይ “ቻይና የኢትዮጵያን የፈጠራ ዘርፍ ለማጠናከር፣ ችሎታን ለማዳበር የስልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገች ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ትልቅ ፌስቲቫል ነው ያሉ ሲሆን ይህ ፌስቲቫል ከልምድ ልውውጡ በላይ በሁለት ሀገራት መካከል የባህል፤ ታሪክ እና የፈጠራ ትብብርን የሚያጠናክር እንደሆነ ገልጸዋል።