“ነፃነት”ለአንድ ቀን የሚቆየው የሥዕል ኤግዚብሽንና ጨረታ ህዳር 26 ይካሄዳል።ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በቅርቡ …

Reading Time: < 1 minute
*
“ነፃነት”

📌ለአንድ ቀን የሚቆየው የሥዕል ኤግዚብሽንና ጨረታ ህዳር 26 ይካሄዳል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በቅርቡ በስዊድን ለሚያደርገው ህክምና ወጪን ለመሸፈን ነጻነት የተሰኘ የሥዕል ኤግዚብሽን ማዘጋጀቱን በዛሬው እለት በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ጋዜጠኛ ኤደን ገብረህይወት እና ጋዜጠኛ ራኬብ ሐብቴ በጋራ ባሰናዱት እና በመጪው ሐሙስ ሕዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በላሊበላ አዳራሽ በሚካሄደው የሥእል አውደ- ርዕይና የሥዕል ጨረታ ፕሮግራም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ሰዎችና ሠአሊዎች ይገኛሉ ተብሏል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ከ17 አመት ዕድሜው ጀምሮ አንኪሉዚንግ ስፖንዳላይተስ የተሰኘ አጥንት ውስጥ ያለ ፈሳሽን የሚያደርቅ ህመም አጋጥሞት ሙሉ በሙሉ ሰውነቱ እንዳይነቀሳቀስ ያደረገው ሲሆን በቅርቡ በስዊድን ሀገር ለሚያደርገው የጉልበት ንቅለ ህክምና ወጪን ለመሸፈን “ነጻነት” የተሰኘ የስዕል ኤግዚብሽን ተዘጋጅቷል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ እንደገለፀው ከዚህ የሥእል አውደ- ርዕይና የስእል ጨረታ ፕሮግራም የሚገኘው ገቢ በቅርቡ ስዊድን ሀገር ለሚያደርገው የጉልበት ንቅለተከላ የሚውል ሲሆን አጠቃላይ የህክምና ወጪው ሶስት ሚልየን ብር እንደሆነ ተገልጿል።
164030cookie-check“ነፃነት”ለአንድ ቀን የሚቆየው የሥዕል ኤግዚብሽንና ጨረታ ህዳር 26 ይካሄዳል።ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በቅርቡ …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE