የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና ተጠናቀቀየአዲስ አበባ…

Reading Time: < 1 minute
*
የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን፤ የ2016 ዓ.ም 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠናና ዓለማቀፍ የፕሮ ቴኳንዶ የመጀመሪያ ራስን መከላከል ስልጠና በወወክማ አዳራሽ ላለፉት 15 ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

ከ28 በላይ ሰልጣኞች በተሳተፉበት በዚህ ስልጠና ላይ
ሳኦል ኹነቶች ለአራት ሰልጣኞች የስፖርት ማዘውተሪያ ያመቻቸ ሲሆን በቅርቡ ፒያሳ አካባቢ በኮሪደር ልማት የስፖርት ማዘውተሪያ ለፈረሰበት አንድ ወጣት በቀጣይ ቦታ ለማመቻችች በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሐግብር ላይ ቃል ተገብቶለቷል።

የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ማስተር ሃይለየሱስ ፍስሃ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት የተሰጠው 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና፣ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሠጠው የመጀመሪያ ኮርስ ነው ብለዋል።

በዛሬው እለት ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የተሰጣቸው የእውቅና የምስክር ወረቀት የኦን ላይን ሲሆን ፤ ምስክር ወረቀቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ እንደተደረገ ተገልጿል።
86740cookie-checkየአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና ተጠናቀቀየአዲስ አበባ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE