ዶዳይ የኤሌክትሮኒክ ሞተር አምራች እና አከፋፋይ ድርጅት ለመጀመሪያዎቹ 250 ደንበኞ የታርጋ ወጪን ሸፈነ።
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ የካቲት 1፣ 2017 ዓ.ም —ዶዳይ የኤሌክትሮኒክ ሞተር አምራች እና አከፋፋይ ድርጅት ለመጀመሪያዎቹ 250 ደንበኞች የታርጋ ወጪን በመሸፈን አዲስ ጅምሮ መዘርጋቱን አስታውቋል። ይህ እርምጃ የኤሌክትሮኒክ ሞተርባይክ ባለቤትነትን በኢትዮጵያ የበለጠ ተደራሽ በማድረግ እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ብሩህ የወደፊት መንገድን ከፍቷል።
ዶዳይ ደንበኞቹ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ280 በላይ አባላት ያሉት የኤሌትሪክ ሞተር ብስክሌት ባለቤቶች ማኅበር በማቋቋም ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤቶች የሚሰጠውን የታርጋ ፍቃድ አሰጣጥ ሂደት ለማቀላጠፍ ፈር ቀዳጅ ጥረት አድርጓል። ማህበሩ በሚያደርገው ዘላቂ ትራንስፖርት ሽግግር፣ የባለቤትነት ልምድን የበለጠ ለማሳደግ እና አባላቱ ተገቢውን የከተማ ትራፊክ ደንብ ተከትለው አገልግሎት እንዲያገኙም ሆነ እንዲሰጡ ድጋፍ ይሰጣል።
የዶዳይ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዩማ ሳሳኪ “ከ750 በላይ ኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን ሽያጭ በመፈፀማችን በጣም ደስተኞች ነን። የደንበኞቻችንን የታርጋ ወጪ በመሸፈን እና ይህን ማህበር እንዲመሰረቱ በማድረግ የባለቤትነት ሂደቱን ከማቅለል ባለፈ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ተንቀሳቃሽነት አብዮት እያራመድን ነው። አላማችን ዘላቂ ትራንስፖርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ነው” ብለዋል።
ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ከተሞች የትራንስፖርት መልክዓ ምድር አቀማመጥን እና አካባቢን የማይጎዱ መፍትሄዎችን በማስፈን የዶዳይን ዋነኛ ተልእኮ ያሳያል። ኩባንያው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ፍላጎት ለማሟላት አስተማማኝ የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች እና የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የጋዜጣዊ መግለጫ መርሐግብሩ በዛሬ ዕለት በዶዳይ ዋና መሥሪያ ቤት ተካሄዷል።
ስለ ዶዳይ
ዶዳይ በኢትዮጵያ ቀዳሚ የኤሌክትሪክ ኩባንያ ሲሆን አዳዲስ እና ዘላቂ የትራንስፖርት መፍትሄዎችን ለማቅረብ ቁርጠኛ የሆነ ኩባንያ ነው። ዶዳይ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና ደንበኞችን ያማከለ አገልግሎት ላይ ትኩረት በማድረግ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ በኢትዮጵያ የከተማን እንቅስቃሴን ለመቀየር እየሰራ ይገኛል።
ለተጨማሪ መረጃ ወይም ስለ ዶዳይ ኤሌክትሪክ ሞተሮች ለመጠየቅ ፡
ህሊና ለገሰ
ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ
ስልክ፡ +251-911-482216
ኢሜይል፡ Hilinal@dodai.com