500,000.00 (ግማሽ ሚሊዮን ብር) አበርክተዋልተጨማሪ ይመል“መቄዶንያን የመደገፍ፣ የመርዳት፣ የበረከት፣…

Reading Time: < 1 minute
500,000.00 (ግማሽ ሚሊዮን ብር) አበርክተዋል

ተጨማሪ ይመል“መቄዶንያን የመደገፍ፣ የመርዳት፣ የበረከት፣ የበጎነት፣ በአረጋውያን የመመረቅ ታላቅ እድል ነው። ስለዚህም 500,000.00 ( ግማሽ ሚሊዮን ብር) ለግሰናል” ~ የብላክ ፐርል መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ብርሃን መሀመድ ሰይድ

አያይዘውም ሁላችንም እንሳተፍ፣ ከበረከቱ እንቋደስ።
ደግ ልባችሁን ይዛችሁ ኑ! – ብለዋል አቶ ብርሃን መሀመድ ሰይድ።



ታሪካዊ ዳራ
ብላክ ፐርል በሰበአዊነት መንገድ

ብላክ ፐርል ከዚህ ቀደም በመቄዶንያ  የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን  መርጃ  ማዕከል የምሳ ግብዣ አደርጓል።

ከተመሠረተ ስምንት አመታትን ያስቆጠረው ብላክ ፐርል በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን  መርጃ  ማዕከል የድርጅቱን ሠራተኞች በማስተባበር የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ምሳ፤ ማዕድ የማጋራት መርሐግብር ማድረጉ ይታወሳል።

በዚያን ጊዜ …
አቶ ብርሃን መሀመድ ሰይድ እንደተናገሩት፤ “የብላክ ፐርል ሠራተኞች እና የማኔጅመንት አባላት ብቻ አይደለንም፤ ክቡራት ደንበኞቻችን፤ ደጋግ ልቦችን ይዘን ለበጎ አድራጎት መቄዶኒያ መጥተናል። ለአገር እና ለሕዝብ ከቃል በላይ በተግባር ( አነሰ፤ በዛ ) ሳንል ግዴታችንን ለመወጣት መጥናል። ለአገር እና ለሕዝብ በጎ ሥራ ለማበርከት ከልባችን ጋር፤ ከደንበኞቻችን ጋር እንቀጥላለን። ” ብለዋል።

እንሆ ዛሬ ላይ ቃላቸውን በተግባር አረጋግጠዋል።

ደግ ልባችሁን ይዛችሁ
ኑ … ፤ ለበጎ አድራጎት ቀጠሮ አትውሰዱ። ዛሬን ለበጎነት ያዉሉ ! – ሲሉ  ለአገር እና ለሕዝብ ጥሪ አሰምተዋል።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር  በአሁኑ ሰዓት ከ8ሺ በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችን በተለይም እራሳቸውን ችለው መንቀሰሳቀስ፣ መመገብ እና መፀዳዳት የማይችሉ አረጋውያንንና አዕምሮ ሕሙማንን ከአዲስ አበባ  ጎዳናዎች ላይ በማንሳት የመጠለያ፣ የምግብ፣ የልብስ፣ የሕክምና አገልግሎትና ቤተሰባዊ ፍቅር በመስጠት ደጋፊና ጧሪ የሌላቸው ኢትዮጵያውያንን እየረዳ ይገኛል፡፡

በቅርቡም አዲስ አበባ የሚገኘውን ማዕከል ጨምሮ በኢትዮጽያ ውስጥ የሚገኙ 44 ማዕከላት ከ7,500 በላይ አረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት ጎዳና አንስቶ በማገዝ ላይ ይገኛል።

ዶ/ር ቢኒያም በለጠ መቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማኅበር  አዲስ አበባ ሐያት አካባቢ በሚገኘው የማዕከሉ ቅጥርም ጊቢው ውስጥ ዘመናዊ እና ሁለ ገብ ህንጻ በማጠናቀቅ ላይ ሲገኝ ማዕከሉን ህብረተሰቡ እንዲጎበኝ እና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል።

የመቄዶኒያ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ስርጭት
ከዛሬ ጀምሮ ይሳተፉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
በ Seifu on EBS YouTube

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!
173920cookie-check500,000.00 (ግማሽ ሚሊዮን ብር) አበርክተዋልተጨማሪ ይመል“መቄዶንያን የመደገፍ፣ የመርዳት፣ የበረከት፣…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE