በተጻፈ ውል ደግሞ በዓመት 12 ሚሊዮን ብር ኮስሞ ትሬዲንግን (ባለዘጠኝ ወለል ሕንፃ) ለቻይናዎች እንዲሸጡ እንዳስፈረሟቸው፣ ድርጅቱ ግን ከእሳቸው ጋር ሦስት ባለድርሻዎች እንዳሉት (ሁለቱ ልጆቻቸው መሆናቸውን ገልጸዋል) ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ብይኑ ይገልጻል፡፡ አቶ ኃይለየሱስ ሦስት ገጽ ዝርዝር የምስክርነት ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ መስጠታቸውንም ሰነዱ ያብራራል፡፡ ሌሎቹ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችም አጠር አጠር ያለ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተው፣ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን አሰምቶ ማጠናቀቁን ብይኑ ይገልጻል፡፡
ፍርድ ቤቱም የቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማየት፣ ተከሳሾቹ ክሱን ሊከላከሉ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚል ጭብጥ ይዞ መዝገቡን መመርመሩን ብይኑ ይጠቁማል፡፡
ፍርድ ቤቱ መጀመሪያ ወ/ሮ አዜብ፣ አቶ ተመስገንና አቶ አደፍርስ የተባሉት ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ) እና አንቀጽ 676 (2ሀ) ድንጋጌን ተላልፈው፣ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፣ የድርጅቱን ሕንፃ ለባንክ መያዣ በማድረግ ገንዘቡን ለግል ጥቅማቸው በማዋል ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የቀረበውን ክስ መርምሯል፡፡
አንድ ወንጀል ተፈጸመ የሚባለው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌን ማለትም ሕጋዊ፣ ሞራላዊና ግዙፍ የፍሬ ነገሮች ተሟልተው ሲቀርቡ መሆኑን በብይኑ የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ እነዚህን ሦስት መሠረታዊ ፍሬ ነገሮች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 675 (1) ድንጋጌ መሠረት ተሟልተው መገኘት እንዳለባቸው በሰበር መዝገብ ቁጥር 118084 አስገዳጅ ትርጉም እንደተሰጠባቸውም አብራርቷል፡፡
በክሱ እንደተገለጸው ተከሳሾቹ ድርጅቱ የተበደረውን ገንዘብ ለግላቸው ጥቅም አውለዋል የሚል ሲሆን፣ ኮስሞ ትሬዲንግ በተፈረመ የአክሲዮን ሽያጭ ውል ለወ/ሮ አዜብና ለቦስተን ሪል እስቴት የተላለፈ መሆኑን፣ ድርጅቱን በማስያዝ ብድር ተወስዷል የተባለውም ለወ/ሮ አዜብ የተላለፈ ሕንፃ መሆኑን የዓቃ ሕግ ምስክር መናገራቸውን ብይኑ ያብራራል፡፡ የዓቃቤ ሕግ አንደኛ ምስክር የሆኑት አቶ ኃይለየሱስም የአክሲዮን ድርሻ ማስተላለፋቸውንና ሕንፃ ሽያጭም ማከናወናቸውን መመስከራቸውንና እሳቸው በተለያዩ ተፅዕኖ ውስጥ ሆነው እንደፈጸሙ ቢመሰክሩም፣ በሌላ የፍትሐ ብሔር ክስ የአክሲዮን ሽያጭ ውል የተደረገው በተፅዕኖ አለመሆኑ ውሳኔ እንደተሰጠበት ፍርድ ቤቱ በብይኑ ጠቅሷል፡፡
ተከሳሻቹ በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት ለአበዳሪው ባንክ ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ ሕጉንና ሥርዓቱን በመከተል በባንክ የብድር ፖሊሲ መሠረት የተበደሩ መሆኑን በከሳሺ ዓቃቤ ሕግ ሁለተኛና ሦስተኛ ምስክሮች ከመመስከሩም በተጨማሪ፣ ለመደበር ‹‹ሥልጣን የላቸውም›› የሚል መከራከሪያ አለመቅረቡን ፍርድ ቤቱ በብይኑ አብራርቷል፡፡ በብድር የተገኘውም ገንዘብ ድርጅቱ (ኮስሞ ትሬዲንግ) ቀድሞ ለተበደረው ዕዳ የተከፈለ ስለመሆኑም ሰነድ መቅረቡንና የኮስሞ ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትና የዓቃቤ ሕግ ስምንተኛ ምስክር መመስከራቸውን፣ ድርጅቱ አሁንም ተጨማሪ ዕዳ እንዳለበት መናገራቸውን ፍርድ ቤቱ አክሏል፡፡ በሌላ በኩል ንብረትነቱ የኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው የተባለው ሆቴል ኪራይ ገቢና የትራክተር ሽያጭ ገንዘብን በሚመለከትም፣ ንብረትነቱ ለተከሳሾች የተላለፈ መሆኑንና ኪራዩንም ሆነ ሽያጩን በሚመለከት የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ አለማቅረቡን ፍርድ ቤቱ በብይኑ ገልጿል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች አስይዘው ተበድረዋል የተባለው ሕንፃም ሆነ ድርጅቱ ሕጉን ጠብቆ ለተከሳሾች (ለወ/ሮ አዜብና ቦስተን ሪል እስቴት) የተላለፈ ከመሆኑ አንፃር፣ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል የሚያስብል ባለመሆኑ ወ/ሮ አዜብና አቶ ተመስገን ከቀረበባቸው ከባድ እምነት ማጉደል ወንጀል ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌ መሠረት በነፃ መሰናበታቸውን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን ገልጿል፡፡
የባንክ ሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው የባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 3(1) እና አንቀጽ 58(1 እና 3) እንዲሁም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀ እና ለ) እና አንቀጽ 34 ድንጋጌዎችን በመተላለፍ፣ አቶ ተመስገን፣ ወ/ሮ አዜብና አቶ አደፍርስ የባንክ ሥራ ሠርተዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ፣ ዓቃቤ ሕግ በሰዎች ምስክርነትም ያላስረዳና የቀረበም የሰነድ ማስረጃ ባለመኖሩ፣ ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌ መሠረት በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱ በሰነዱ ተብራርቷል፡፡
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀል ክስን በሚመለከት፣ ከላይ ቀርቦ ከነበረው ከባድ የእምነት ማጉደል ክስ ጋር የተያያዘ መሆኑንና ብይን እንደሰጠበት ፍርድ ቤቱ ጠቅሶ፣ ወ/ሮ አዜብ ከውጭ አገር ገንዘብ ስለመሰብሰባቸውም ሆነ ቦስተን ሪል እስቴት ለተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት የተቋቋመ ስለመሆኑ የቀረበ ሰነድ ማስረጃ አለመኖሩን ጠቅሶ፣ አቶ ተመስገን፣ ወ/ሮ አዜብና አቶ አደፍርስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 141 ድንጋጌ መሠረት በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ በብይኑ መጨረሻ ላይ እንደገለጸው፣ በአጠቃላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው ክሶች በሰውም ሆነ በሰነድ ሊረጋገጡ ባለመቻላቸው፣ ሁሉም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 141 ድንጋጌ መሠረት በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/140462/

ከኮስሞ ትሬዲንግ ጋር በተያያዘ በከባድ እምነት ማጉደልና በሌሎች ወንጀሎች የተከሰሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች በነፃ ተሰናበቱ – ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best And Reliable…
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ)፣ አንቀጽ 676 (2ሀ)፣ አንቀጽ 34፣ አቀንጽ 702 (1) እና 703 (1)፣ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 3(1) እና አንቀጽ 58 (1 እና 3)፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 (1ሀ እና