የት/ቤቶች ፌስቲቫል በአዲስ አበባ
ከ500 በላይ ት/ቤቶች የሚሳተፉበት ልዩ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው።
ፌስቲቫሉን ቁርንፉድ ዲጂታልስ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጋራ አዘጋጅተውታል።
በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከትምህርት ቤቶች ባሻገር በትምህርት ላይ የሚሰሩ ተቋማት ተማሪዎች እና ወላጆች ይሳተፋሉ ተብሏል።
ይህ ፌስቲቫል በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል ነው የተባለው።
በፌስቲቫሉ ት/ቤቶች በየተቋሞቻቸው በትምህርት ጥራት፣በተማሪዎች ምገባ በከተማ ግብርና እንዲሁም በሁለንተናዊ የትምህርት አገልግሎቶች የሚሰሯቸውን ስራዎች ለጎብኘዎች ያቀርባሉ ተብሏል።
ፌስቲቫሉ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያመጣ ነው የተገለጸው።
በፈረስቲቫሉ ከሚቀርቡ የኤግዚቢሽን ጉብኝቶች ባሻገር ለተማሪዎች ለመዝናኛ የመጫወቻና የመመገብያ ስፍራዎች እንደተዘጋጀ ነው አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ የገለጹት።
በፌስቲቫሉ ለመሳተፍ ለተማሪዎች በነጻ ሲሆን ለመቄዶኒያ ገቢ የሚሆን ወላጆች በልጆቻቸው ስም 100 ብር ይከፍላሉ ተብሏል።