ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን አርቲስት ይገረም ደጀኔን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን በዛሬው ዕለት አርቲስት ይገረም ደጀኔን ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን የኩባንያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በይፋ መሾሙን አስታውቋል።
በበዛሬው እለት በተካሄደው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ እንደተገለጸው፣ ይህ የአምባሳደርነት ስምምነት አርቲስት ይገረም ደጀኔ ለኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ማለትም በቴሌቪዥን፣ በቢል ቦርዶች እና በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የማስታወቂያ ስራዎችን እንዲሰራ ያስችለዋል።
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን የተለያዪ ሞዴሎችን በመቅረጽ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት እያደረገ እንደሚገኝ የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ዋና ስራ እስፈጻሚ አቶ ግሩም ይልማ የገለጹ ሲሆነሰዘፈዠዠወደ ገበያው ከገባበት ጊዜ አንስቶ በአንድ አመት ከስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ በስድስት የተለያዩ ቦታዎች እና በባህርዳር ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የቤት ባለቤት ማድረግ ችሏል።
በእለቱ በተገለጸው መረጃ መሰረት ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን እስካሁን ድረስ ሁለት ጊዜ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ያከናወነ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 20,000 የሚደርሱ አባላት አሉት። ከዚህም በተጨማሪ “ኪ መንደር” የተሰኘ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
የአርቲስት ይገረም ደጀኔን የብራንድ አምባሳደር ሆኖ መሾም ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ለህብረተሰቡ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ተደራሽነቱን በማስፋት ብዙ ዜጎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
X