አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ጥር፣ 2024 – በአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ያንጎ ግሩፕ አካል የሆ…

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ጥር፣ 2024 – በአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ኢትዮጵያ አዲሱን
‘ኮምፎርት ክላስ’ የተሰኘ የጉዞ አገልግሎት አስተዋውቋል።

የዚህ አገልግሎት የመነሻ ታሪፍ 100 ብር ብቻ ሲሆን፣ አዲሱ ታሪፍ ለተሳፋሪዎች የዘመነ የጉዞ ልምድ በመስጠት፣ የተሳፋሪዎችን ፍላጎትን ለማሟላት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ከፍተኛ ደረጃ የተሰጣቸውን እና የአየር ማቀዝቀዣ አማራጭ ያላቸውን መኪኖች ያሰማራው ‘የኮምፈርት ክላስ’ ለተሳፋሪዎች የበለጠ የተስማማ እና ምቹ ጉዞን አቅምንባማከለ መልኩ እንዲጠቀሙ አቅርቧል።

የ‘ኮምፎርት ክላስ’ አዳዲስ እና ምቹ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ፍላጎት ባላቸው ደንበኞች የቀረበ ቀጥተኛ
አስተያየት ተመርኩዞ የተጀመረ አገልግሎት ነው። ያንጎ ይህንን ፍላጎት ለሟሟላት አገልግሎቱን በጥንቃቄ ነድፎ ለተሳፋሪዎች 92 ብር
ከሆነው ከኢኮኖሚ ታሪፍ ትንሽ ከፍ በማድረግ በ100 ብር አቅርቧል። በኢትዮጵያ ሁለት ታሪፎች ያሉ ሲሆን እነሱም ኢኮኖሚ እና
ኮምፈርት አገልግሎቶች ናቸው።

አገልግሎቱ ምቾት ያላቸውን ጉዞዎች ከዘመናዊ ተሸከርካሪዎች ጋር ያጎላበተ ሲሆን ይህን አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተሽከርካሪዎች
በ2018 እና ከዚያ በኋላ የተመረቱ ናቸው። በተጨማሪም፣ በ’ኮንፎርት ክላስ’ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ አየር ማቀዝቀዣ
የሚኖረው ሲሆን፣ ይህም ተጠቃሚዎች ምቹ አካባቢን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

እነዚህ ጉዞዎች፣ ልዩ አገልግሎት ለመስጠት በሚተጉ ከፍተኛ ደረጃ በተሰጣቸው አሽከርካሪዎች የሚነዱ ሲሆኑ፣ ይህም ምቾቱ ከፍ ያለ የጉዞ ልምድ ለሚፈልጉ ደንበኞች ተመራጭ ያደርገዋል።

በኢትዮጵያ የያንጎ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይቅናአለም አበበ እንዳሉት ‘’የኮምፎርት ክላስ ጅማሮ ኩባንያችን በሀገሪቱ ላይ ያለው
የተሽከርካሪ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ልዩነትን ለመፍጠር በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ሆኖ ይቀመጣል። ደንበኞቻችንን
በመረዳት ለፍላጎታቸው ከአኗኗር ዘይቤያቸው ጋር የተጣጣሙ አገልግሎቶች እንሰጣለን” ያሉ ሲሆን አክለውም “ያንጎ ለተሳፋሪዎቹኪሳቸው ሳይጎዳ በ‘ኮምፎርት ክላስ’ ጥራት ያለው አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ አንዲያገኙ ያደርጋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በተሽከርካሪ
አገልግሎት ላይ አዲስ ዝማኔ በመጀመራችን ኩራት ይሰማናል፣ ተሳፋሪዎችንም በኮምፎርት ክላስ ለማገልገል እንጠባበቃለን” ሲሉ
ተናግረዋል።

ያንጎ ለተሳፋሪዎቹ በቀጥታ በያንጎ መተግበሪያ በኩል በሚመርጡት ታሪፍ እንከን የለሽ
የ’ኮምፎርት ክላስ’ ጊዞዎችን አንዲያገኙ
አድርጓል።

ይህንን የተሻሻለ አገልግሎት አስመልክቶም ያንጎ ለመጀመሪያው የ’ኮምፎርት ክላስ’ ጉዞ ተጠቃሚዎች የ10% ቅናሽ እያደረገ
ሲሆን እስከ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ETCOMFORT” የሚለውን የማስተዋወቂያ ኮድ በመጠቀም ቅናሹን ማግኘት ይቻላል።

ያንጎ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለመፍጠር እና ለማሻሻል የሚያደርገው ጥረት ዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂን የአካባቢ ፍላጎቶችን ወደሚያሟሉ
መፍትሄዎች የመቀየር ትልቁን ተልዕኮውን ያንፀባርቃል። የ‘ኮምፎርት ክላስ’ መጀመር ኩባንያው የኢትዮጵያውያንን የዕለት ተዕለት ኑሮ
ከፍ የሚያደርጉ የተሻሻሉ የመንቀሳቀሻ አማራጮችን ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን ያረጋግጣል፡፡

መጨረሻ ስለ ያንጎ ያንጎ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤቱን በዱባይ ያደረገ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙ
ቴክኖሎጂዎችን ወደ ዕለት ተዕለት አገልግሎቶች በመቀየር ለአካባቢው ማኅበረሰቦች የሚያቀርብ ድርጅት ነው።

ለፈጠራ ባለው የማያወላውል ቁርጠኝነት፣ ከአለም ዙሪያ መሪ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያለምንም እንከን ወደ የተቀናጀ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች እየቀየረ ይገኛል። ተልእኳችን በአለም ፈጠራዎች እና በአከባቢ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ ፣ግንኙነቶችን ማጎልበት እና የዕለት ተዕለት የኑሮ ልምዶችን ማሻሻል ነው።

የያንጎ ባለብዙ-ተግባር መተግበሪያ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅባሉ ከ20 በላይ አገሮች ውስጥ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን ይሰጣል። የያንጎ ባለ ብዙ ቋንቋ መተግበሪያ በአንድሮይድ እና አይኦኤስ (iOS) ላይ በነጻ ይገኛል፡፡
174280cookie-checkአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ጥር፣ 2024 – በአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ያንጎ ግሩፕ አካል የሆ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE