ኪ ሃውሲንግ ተመዝጋቢዎች ለ174 እድለኞች የቤት እጣ ወጣላቸውኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ለአራተኛ ጊዜ ባ…

Reading Time: < 1 minute
*
ኪ ሃውሲንግ ተመዝጋቢዎች ለ174 እድለኞች የቤት እጣ ወጣላቸው

ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ለአራተኛ ጊዜ ባካሄደው የቤት እድለኞች መለያ መርሃ ግብር በትናትናው እለት ለ174 እድለኞች እጣ ወጥቶላቸዋል።

መርሃ ግብሩ ትናንት ባለ እድለኞቹ በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን፥ በ83 ሺህ 145 ብር ቅድመ ክፍያ እና በወር ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ በቁጠባ ለሚሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤትነት እድል እየሰጠ ይገኛል።

ኩባንያው ወደ ገበያው ከገባ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት በሆነ ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ በስድስት የተለያዩ ቦታዎች እና በባህርዳር ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የቤት ባለቤት እንዳደረገ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም 20 ሺህ የሚደርሱ አባላት እንዳሉት የገለጸው ኪ ሃውሲንግ፥ “ኪ መንደር” የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን በእጣ አወጣጥ መርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።
184790cookie-checkኪ ሃውሲንግ ተመዝጋቢዎች ለ174 እድለኞች የቤት እጣ ወጣላቸውኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ለአራተኛ ጊዜ ባ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE