ሁልጊዜ ታክሲ ውስጥ ሒሳብ ሰብስቡልኝ ሲል ሁለት ነገር ወደ አእምሮዬ ይመጣል
አንደኛው ሹፌሩን መተባበር መልካም መሆኑን
ሁለተኛው ግን ቆይ ለምን አንድ ዜጋ ይዞ አይሠራም?
ይህ ሰው እኮ ሁሌም ገንዘብ ስለምንሰበስብለት አብሮት ሊሠራ የሚችል የአንድ ወጣት ዜጋ ሥራ ቀምተን ሥራ አጥ አድርገናል ማለት ነው።
እኔ ዛሬ ሒሳብ በመሰብሰብ ስለተባበርሁት ነገ ሌላው ሰው እንዲተባበረውም መዘዝ እያመጣሁበት ነው ያ ሰው ደግሞ ሒሳብ ሰብስቦ ስለማያውቅ እስከመጨነቅ ይደርሳል። ከዚህም አልፎ ከሌላ ሰው ጋር እስከመጣላት ይደርሳል አብረን ተሳፍረን አንዱ ሒሳብ ሰብሳቢ ሆኖ አብረውት ከተሳፈሩት ሰዎች ጋር እስከመጣላት ሲደርሱ አይቻለሁ!
ብር ሰብስቡልኝ ገመዱን ጎትተ፣ ሽቦውን ንካው፣ ወደ ታች ተጫንና ክፈተው፣ የት ናችሁ ? ብለህ አስገባልኝ ወዘተ የሚሉ መመሪያዎችን እያስተላለፈ፣ ዝርዝር ለመስጠት በሁለት እጁ ብር እየቆጠረም መኪና እያሽከረከረ፣ ሒሳብ አብሮ እየሠራ አብረነው የምንሠራለት ሹፌር እኛ ስላገዝነው ብቻ የአንድ ወጣት ዜጋ ሥራ የቀማን ይመስለኛል።
እኛ ሹፌሩን እየተባበርን ነው መልካም ተግባር ነው ግን የአንድ ዜጋ ሥራ እየቀማን ነው እኒህ ያለ እረዳት የሚሠሩ ሹፌሮችን ውጤታማነት የሚያዩ ሌሎችም የታክሲ ሹፌሮች አሁን አሁን ያለ ረዳት መሥራቱን እየተቀላቀሉ ታክሲዎች ሁሉ ረዳት እየተዉ ሕዝቡ እረዳት እየሆነ ነው 2 ሺህ ታክሲዎች ያለ ረዳት ሠሩ ማለት 2ሺህ ወጣቶች ሥራ አልባ ሆኑ ማለት ነው በዚህ ውስጥ ደግሞ ሌላ ቤተሰብ አለ
በእርግጥ አንዳንድ ሹፌሮች ደግሞ ለምን ረዳት አይኖራችሁም ሲባሉ የሚነግሩን ምላሽ በቃ አልቻልናቸውም ያጭበረብሩናል የነዳጅ ዋጋ ምናምን ይላሉ።
ምንም ቢሆን በአግባብ ሠርቶ መለወጥ እንጂ ትርፋማነትን በተሳሳተ መንገድ ለማግኘት መሞከር ስሕተት ነው ለአሽከርካሪና ለተሳፊሪዎችም ስልክ እያወሩ ከመንዳት በላይ አደጋ ያስከትላል የዜጋ ሥራ አጥነትንም ያስፋፋል ብዬ ነው የማስበው።
እኔ ሁሌም ገንዘብ ሰብስቡልኝ የምትለዋን ንግግር ስሰማ እኒህ ሁለት ሐሳቦች ወደ አእምሮዬ መምጣታቸው አይቀርም
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
Via Zelalem Hasebe