ከኮስሞ ትሬዲንግ ጋር በተያያዘ በከባድ እምነት ማጉደልና በሌሎች ወንጀሎች የተከሰሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች በነፃ ተሰናበቱ
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ)፣ አንቀጽ 676 (2ሀ)፣ አንቀጽ 34፣ አቀንጽ 702 (1) እና 703 (1)፣ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 3(1) እና አንቀጽ 58 (1 እና 3)፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 (1ሀ እና 2መ) እና አንቀጽ 33 (1ሀ) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለ ድርጅት ላይ ከባድ የእምነት ማጉደል፣ ፈቃድ ሳይኖራቸው በባንክ ሥራ ላይ መሰማራት፣ በሕገወጥ ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በሌላ ሰው ጥቅም የሥራ አመራር ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀሎች ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ አራት ግለሰቦችና ሦስት ድርጅቶች የተመሠረተባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ችሎት ባለፈው ሳምንት በሰጠው ብይን በነፃ ያሰናበታቸው ተከሳሾች ወ/ሮ አዜብ ምሕረተዓብ፣ አቶ ተመስገን ይልማ፣ አቶ አደፍርስ ሀብቴ፣ አቶ መስፍን አስማማው፣ ጄጄ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ቲቲኤች ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና ቦስተን ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችን፣ የባንክ ሥራ አዋጅ ድንጋጌዎችን፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣን አዋጅ ድንጋጌዎችን ተላልፈዋል በሚል፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መሥርቶት የነበረው ክስ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በግለሰቦቹና ድርጅቶቹ ላይ የመሠረተውን ክስ በሰው ምስክሮችም ሆነ በሰነድ ማስረጃዎች በብቃት ማስረዳት አለመቻሉን በብይኑ ጠቅሶ፣ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌ መሠረት በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን መስጠቱን አስታውቋል፡፡
ዓቃቤ ሕግ ለክሱ ዋና መነሻ ያደረገውና ክስ የመሠረተው፣ ወ/ሮ አዜብና አቶ ተመስገን የተባሉት ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፣ የግል ተበዳይይ የሆነው የኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሳለ፣ የዋና ሥራ አስኪያጁ ሙሉ ሥልጣን እንዲኖራቸው አድርገዋል፡፡ በዚህም ራሳቸው ለራሳቸው በሰጡት ሹመት ድርጅቱን እንዲያስተዳድሩ በማድረግ፣ ድርጅቱን በማስያዝ 61 ሚሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በመበደር፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ቀደም ብሎ ከኅብረት ባንክ የተበደረውን 21 ሚሊዮን ብር መክፈላቸውን የብይን ሰነዱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ ቀሪውን 40 ሚሊዮን ብር ወደ ኮስሞ ትሬዲንግ የሒሳብ ቋት ገቢ ካደረጉ በኋላ፣ ለድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አሥር ሚሊዮን ብር ማበደራቸውንና ተጨማሪ 32,500,000 ብር ደግሞ ንብረትነቱ የወ/ሮ አዜብ ለሆነውና አቶ ተመስገን በውክልና ለሚያስተዳድሩት ጄጄ ፕሮርቲ ድርጅት ማስተላለፋቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ይዘረዝራል፡፡ የወ/ሮ አዜብ ድርጅት ለሆነውና እራሳቸው ለሚያስተዳድሩት ቦስተን ሪል እስቴትም 7000,000 ብር ማስተላለፋቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡ ከብድሩ ላይ በተለያዩ ቀናት 11,014,000 ብር እና 5000,000 ብር ደግሞ ንብረትነቱ የአቶ ተመስገን ለሆነው ቲቲኤች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላለበት የባንክ ብድር ክፍያ ማዋላቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ከባንክ የተበደሩትን ቀሪ ገንዘብ በግል ግንኙነት ላላቸው በክፍያ መስጠታቸውንም አክሏል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው አቶ ተመስገን ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ‹‹ዋን ሃው›› ለተባለ ሆቴል ያከራየውን ሕንፃ ገቢ 14,400,000 ብርና ከአንድ ግሬደር ተሽከርካሪ ሽያጭ የተገኘ 1,410,000 ብር ለግል ጥቅማቸው ማወዋላቸውን በመግለጽ፣ ኮስሞ ትሬዲንግን በመመሥረቻ ጽሑፉ መሠረት በሕጋዊ የንግድ ተግባር እንዲመሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ የድርጅቱን ሕንፃ ለባንክ መያዣ በማድረግና ከፍተኛ ገንዘብ በመበደር ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው፣ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸው ነበር፡፡
ዓቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዜብ፣ አቶ ተመስገንና አቶ አደፍርስ የባንክ ሥራን በመተካት ፈቃድ ሳይኖራቸው በተለይ ወ/ሮ አዜብ በአሜሪካና አውሮፓ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ በመሰብሰብ፣ በኢትዮጵያ ብር መንዝረው ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የማስተላለፍ ሥራ መሥራታቸውንና አቶ ተመስገን ደግሞ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው ከቀረቡትና የኮስሞ ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከነበሩት አቶ ገመቹ ዲንቃ ከተባሉ ግለሰብ ጋር በመሆን፣ የተላከው ገንዘብ ወጪ በማድረግ ለተለያዩ ግለሰቦች (ግለሰቦቹ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሆነዋል) መስጠታቸውን ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ በክሱ ዘርዝሮ በማቅረብ፣ ተከሳሾቹ ፈቃድ ሳይኖራቸው የባንክ ሥራ በመሥራት ወንጀል ክስ መሥርቶባቸው ነበር፡፡
ዓቃቤ ሕግ በወ/ሮ አዜብና አቶ ተመስገን ላይ ያቀረበው ሦስተኛ ክስ፣ ተከሳሾቹ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስለውና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት፣ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ተላልፈው ወንጀል ፈጽመዋል የሚል መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡ ተከሳሾቹ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 (1ሀ እና 2መ) ድንጋጌዎችን ተላልፈው፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን እንዲያስተዳድሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ ከአዋሽ ባንክ 61,000,000 ብር በመበደር፣ ገንዘቡን ለግለሰቦችና ድርጅቶች በማዘዋወር፣ ዕዳ በመክፈልና ለተለያዩ ግለሰቦች በመክፈል በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው የማቅረብ ወንጀል መፈጸማቸውን፣ በክሱ በዝርዝር ጠቅሶ ማቅረቡን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን ላይ ገልጿል፡፡
ዓቃቤ ሕግ አቶ መስፍን አስማማው በተባለው ግለሰብ ላይ የመሠረተው ክስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 702 (1) እና 703 (1) ድንጋጌዎችን መተላለፍ፣ ግለሰቡ ለሌላ ጥቅም በሥራ አመራር ላይ ጉዳት የማድረስ ወንጀል ፈጽሟል የሚል ሲሆን፣ ተከሳሹ በውል ግዴታ ተቀብሎ በሥራ አስኪያጅነት በሚመራው ድርጅት (ኮስሞ ትሬዲንግን) በማንኛውም ፍርድ ቤት ከሳሺ፣ ተከሳሺ ወይም ጣልቃ ገብ ሆኖ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲፈጽም ግዴታ የገባ ቢሆንም፣ የግል ተበዳይ (ድርጅቱ) የ50,,000,000 ብር ክስ ተመሥርቶበት ሳለ፣ በፍርድ ቤት ቀጠሮ እያለበት ባለመቅረቡ በድርጅቱ ላይ እንዲወሰንበት በማድረጉ መከሰሱን የክስ ሰነዱ ያብራራል፡፡
ዓቃቤ ሕግ ከላይ በዘገባው ለተዘረዘሩት ክሶች ዘጠኝ ምስክሮችን ፍርድ ቤት አቅርቦ ያሰማ ሲሆን፣ አንደኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት አቶ ኃይለየሱስ መንግሥቱ የተባሉ ምስክር መሆናቸው በብይኑ ተገልጿል፡፡ ምስክሩ በሰጡት ምስክርነትም ከወ/ሮ አዜብ ጋር እንደሚተዋወቁና ገንዘብ ከእሳቸው በአራጣ እየተበደሩ 100,000 ብር እና 200,000 ብር እየጨመሩ ይመልሱ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ከኮስሞ ትሬዲንግ ጋር በተያያዘ በከባድ እምነት ማጉደልና በሌሎች ወንጀሎች የተከሰሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች በነፃ ተሰናበቱ – ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best And Reliable…
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ)፣ አንቀጽ 676 (2ሀ)፣ አንቀጽ 34፣ አቀንጽ 702 (1) እና 703 (1)፣ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 3(1) እና አንቀጽ 58 (1 እና 3)፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 (1ሀ እና