ለ253 ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጣ።

Reading Time: < 1 minute

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከአንድ አመት በፊት ሰርቶ ያስገነባዉን የ10/90 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት የእጣ አወጣጥ ስነስርአት በዛሬው እለት መስከረም 20 ቀን2016ዓ.ም ኮንጎ ሜዳ በሚገኘው ወጣት ማዕከል ተከናውኗል።

ላለፉት ስድስት አመታት ውስጥ ለስድስት ወራት በተከታታይ የቆጠቡ 5328 ነዋሪዎች በእጣው ማውጣት ውስጥ የተካተቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አካል ጉዳተኞች ፣ የመንግስት ሰራተኞችን እና ሴቶችን ታሳቢ በማድረግ ለ253 ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዘመናዊና ግልፅ በሆነ መልኩ ሶፍትዌር በመጠቀም እጣው የማውጣት ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

የድሬደዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በኢንዱስትሪ መንደር ቁጥር 2 ሳይት በአጠቃላይ 358 የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ሲሆን የንግድ ቤቶችና ሱቆች በጨረታ የሚተላለፉ 41 ቤቶች እንዲሁም በመንግስት የሚተላለፉና ለልማት ተነሺዎች የሚሰጥ 10 በመቶ ሲቀነስ 253 ቤቶች በእጣ ለእድለኞች በዛሬው እለት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በተገኙበት ለነዋሪዎች ተላልፏል።

(ጌች ሐበሻ)
59810cookie-checkለ253 ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጣ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE