ግራንድ አፍሪካ ረን እና የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የፊታችን ኦክተበር ወር ላይ ይደረጋል
#Ethiopia | በአሜሪካን ሀገር በየአመቱ የሚካሄደው የግራንድ አፍሪካ ረን እና የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ዘንድሮ ለሰባተኛ ግዜ በዋሽንግተን ዲሲ በቀጣይ ኦክተበር ወር ላይ እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።
በኖቫ ኮኔክሽን በየአመቱ የሚካሄደው እና ዘመናዊ መኪና የሚያሸልመው የግራንድ አፍሪካን ረን የአምስት ኪሎ ሜትር ውድድር በሺዎች የሚቆጠሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በየዓመቱ የሚሳተፉበት ክስተት ሆኗል።
በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ እንደተደረገው ሩጫው ኦክተበር 11 ፣ ለታዋቂ ግለሰቦች እውቅና የሚሰጥበት የሽልማት መርሐግብር ደግሞ በማግስቱ ኦክተበር 12 ቀን 2025 በሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ይካሄዳል።
የኖቫ ኮኔክሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋሻው አብዛ(ዶ/ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተቋማቸው በነዚህ ሁለት ፕሮግራሞች የዲያስፖራ ማህበረሰቡን ማገልገል በመቻሉ ትልቅ ክብር እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
ዶክተር ጋሻው ጨምረው እንደገለጹት የውድድሩ ዓላማ የዲያስፖራውን ማህበረሰብ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በባህል ልውውጥ እና በልዩ ስኬቶች እውቅና በመስጠት ማስተሳሰር መሆኑን አብራርተዋል። ግራንድ አፍሪካ ረን በሺዎች የሚቆጠሩ የዲያስፖራ አባላት በየዓመቱ የሚሳተፉበት የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችን በአንድነት የሚያሰባስብ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው በሌላ በኩል፣ አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በሙያቸው እና በማህበረሰብ አገልግሎታቸው ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች አፍሪካውያን እውቅና የሚሰጥ መድረክ ነው ብለዋል።
ከጋዜጣዊ መግለጫ ጎን ለጎን ኖቫ ኮኔክሽን ከአዳዲስ ድርጅቶች ጋር የአጋርነት ስምምነት ፈፅሟል።
አርቲስት አብርሃም ወልዴን በቅርብ አምባሰደር ያደረገው ጊፍት ሪል ስቴት ጨምሮ አሪፍ ፔይ ከኖቫ ኮኔክሽን ጋር አብረው ለመስራት ስምምነት ሲፈፅሙ ሌላኛው አጋር ሀገር በቀሉ ትጥቅ አምራች ጎፈሬ የዘንድሮ የመሮጫ ቲሸርትን ይፋ አድርጓል።
የኖቫ ኮኔክሽን ግራንድ አፍሪካ ረን ዝግጅት ሲጠናቀቅ ተጨማሪ ለሀገራቸውና ለማህበረሰባቸው በሙያቸው ትልቅ አገልግሎት የሰጡ ግለሰቦች እውቅና የሚያገኙበት የአፍሪካን ኢምፖክት አዋርድ ዝግጅትም አብሮ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የዘንድሮውን የሩጫ እና የሽልማት ፕሮግራም አሌክሳንድሪያ ቶዮታ፣ ዳሸን ባንክ፣ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ ሮሚንግ ሩስተር፣ ጎፈሬ ስፖርትስ፣ አሪፍ ፔይ እና ጊፍት ሪል እስቴት ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች መሆናቸው ታውቋል።
ሁለቱ ፕሮግራሞች ባለፉት አመታት እንደ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ስለሺ ስህን፣ ገንዘቤ ዲባባ ላሉ ብርቅ የኢትዮጵያ አትሌቶች እውቅና ሰጥቷል።
ከዚህም በተጨማሪ እንደ ዝነኛው አርቲስት ኤኮን፣ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ አቶ ግርማ ዋቄ፣ አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ እና አርቲስት አስቴር አወቀ ላሉ ታዋቂ ግለሰቦች እውቅና ሰጥቷል።
ኦክቶበር 11 በሚካሄደው ዝግጅት ላይ ከሚካፈሉ ተሳታፊዎች መካከል እድለኛ የሆነ ባለዕጣ በአሌክሳንድሪያ ቶዮታ የሚቀርበውን የ2025 ቶዮታ ኮሮላ መኪና በዝግጅቱ ማጠናቀቂያ ላይ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ተከናውኖ እንደሚሸለም ታውቋል።
በዚህ ዝግጅት ታላላቅ አትሌቶች እና የኪነጥበብ ባለሞያዎች በክብር እንግድነት እንደሚሳተፉም አዘጋጁ ኖቫ ኮኔክሽንስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስተዋወቀ ሲሆን በሩጫው ላይ ለመሳተፍ እና ለመመዝገብ እና መረጃዎችን ለማግኘት www.africanrun.com ላይ መግባት እንደሚቻል ተገልጿል።