በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በግጭትና በሌሎች ምክንያቶች ከኑሮአቸውና ከሚተዳደሩበት ስራቸው የተፈናቀሉ ሴቶችን የገቢ ማስገኛ ዘርፍ እንዲሰማሩ ለማስቻል ያለመ ኘሮጀክት ይፋ ሆነ።
ታላቁ ሩጫ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከዩ ኤን ዲ ፒ ጋር በቅንጅት በመተባበር በቀጣይ አመት ህዳር ወር ላይ ለ23 ኛ ጊዜ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ውድድር አስመልክቶ በአማራ ፣ በአፋር እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ አንድ ሺ ያክል ለሚሆኑ በግጭት ምክንያት ከስራቸው የተፈናቀሉ እና ስራ ላቆሙ ሴቶችን ገቢ ማስገኛ የሚሆን ለእያንዳዳቸው የ5መቶ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ኘሮጀክት መሆኑን ወይዘሮ ሂሊና ንጉሴ የታላቁ ሩጫ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ለዝግጅታችን ክፍል አሳውቀዋል።
በገቢ ማስገኛ ኘሮጀክቱ በይፋ ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ገዳይ ሚኒስቴር ሚኒስተር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ፣ ዩ ኤን ዲ ፒ ተወካይ አቶ ቱርሀን ሳላህ እና የታላቁ ሩጫ መስራች አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።