ጆይፉል ላይፍ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለሚያከናው ነው የበጎ አድራጎት ስራ ለማገዝ እንዲቻል የተለያዩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ ታዋቂ ሰዎችን ዛሬ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ላይ አምባሳደሮችን ሸመ።
![]()

ጆይፉል ላይፍ ጥቅምት 13 ቀን በ2004 ዓ.ም የተቋቋመ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የማህበራት ማደራጃ ኤጀንሲ 2676 የተመዘገበ ሀገር በቀል የእርዳታ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ሲመሰረት በአዲስ አበባ ከተመረጡ ሁለት ክፍለ ከተሞች ከድሀ ቤተሰቦች በተገኙ 16 ልጆች ስራውን መጀመሩን በዛሬው እለት በተሰጠ መግለጫ ላይ ገልጸዋል።
ጆይፉል ላይፍ የምግብ፣ የትምህርት መርጃ፣ ዩነፎርም፣ የጤና ሽፋን እና የአልባሳት እርዳታ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በ2005 እና በ2006 ከሀዲያ ዞን ጋር በመተባበር 2 የትምህርት ቤቶች ግንባታና 1 የውሃ ጉድጓድ ቆፍሮ አስረክቧል።

ከ2008ዓ.ም ጀምሮ እርዳታ የሚደረግላቸው ልጆች 75 የደረሱ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ልዩ ፍካጎት ካለባቸሁ ህጻናት እና በወላጅ አልባ ህፃናት ፣በኤች.አይ.ቪ የተጠቁ ጨምሮ 104 ልጆችን ይረዳል። በተጨማሪ ከ20 ልዩ ፍላጎት ካላቸው ልጆች የማቆያ አገግሎት እና በመስጠት እና ከ40 ያላነሱ እናቶች እራስን የማሰቻል አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

በዛሬው እለት ጆይፉል ላይፍ አምባሳደር አድርጎ የሾማቸው አቶ ኤባ ተስፋዬ ፣ አርቲስት ናርዶስ አዳነ ፣ አርቲስት ባዩሽ ከበደ ፣ አርቲስት እና የማስታወቂያ ባለሙያ ናትናኤል ግርማ እና ወይዘሮ ሃሊማ አብዱልሽኩር ናቸው።

5552-11cookie-checkጆይ ፉል ላይፍ ቻሪቲ አምባሳደሮችን ሾመno