“ከምንግዜውም በላይ እርዳታችሁን እንሻለን”በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የሚገኘው የባዚ አቡነ…

Reading Time: < 1 minute
*
“ከምንግዜውም በላይ እርዳታችሁን እንሻለን”

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የሚገኘው የባዚ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በአሁን ወቅት ለምዕመናን አገልግሎት ለመስጠት በአስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱን አሳወቀ።

የቤተክርስቲያኑ አሰሪ ኮሚቴ ትናንት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ጥቂት ሰዎች በተገኙበት የገቢ ማሰባሰብያ ማስጀመሪያ መርሀግብር አካሂዷል።

የባዚ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በ1587 ዓ.ም የተመሠረተ ጥንታዊ ቤተ-ክርስቲያን ሲሆን ከግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም በምስራቅ በኩል 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ በመርሐግብሩ ላይ የገዳሙ ታሪክ በቀረበበት ወቅት ተገልጿል።

ቤተክርስቲያኑ በ1953 ዓ.ም የታደሠ ሲሆን ሀገሩ ቆላ በመሆኑ እንጨቱን ምስጥ በልቶት ሲሚንቶው ተፈረካክሶ ቆርቆሮው ዝጎ ቤተ-ክርስቲያኑ አገልግሎት ለመስጠት በአስቸጋሪ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ለቤተ-ክርስቲያኑ በአጥቢያዉና በአዲስ አበባ ኮሚቴ ተቋቁሞ እርዳታ በማሰባሰብና ችግሩን ለሰፊዉ ምዕመናን በመናገርና በማስረዳት በቀጣይ ዋናዉን ቤተክርስቲያን ለማሰራት ፣ ቤተልሔሙን ለማሰራት ፣ እቃ ቤቱን ለማሰራት ፣ አዳራሽ ለማሰራትና ለካህናት መተዳደሪያ ማዘጋጀት የመሳሰሉትን ለማሰራት 7,801,860 (ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ አንድ ሺ ስምንት መቶ ስልሳ ብር) እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።

ስለዚህ በመላው አለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ ቤተክርስቲያኑ ለጀመረው ስራ እንዲያግዝ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000502246287 የባዚ ተክለ ሃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ወይም በስልክ ቁጥር 0911551512 / 0913400914
ተጠይቋል።
169530cookie-check“ከምንግዜውም በላይ እርዳታችሁን እንሻለን”በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የሚገኘው የባዚ አቡነ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE