አዋጭ የአባላት የገና ባዛር ማዘጋጀቱን አስታወቀየአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በንግዱ …

Reading Time: < 1 minute
*
አዋጭ የአባላት የገና ባዛር ማዘጋጀቱን አስታወቀ

የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ አባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና በገበያው ውስጥ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት በተመለከተ የራሱን አስተዋፆ ለማበርከት”የአባላት የገበያ ትስስር ለጋራ እድገት” በሚል መሪ ቃል ከታህሳስ 22 ቀን እስከ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የአዋጭ የአባላት የገና ባዛር በትናንትናው ዕለት ተጀምሯል።

የኅብረት ስራ ማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ አዋጭ ከምስረታው ጀምሮ ላለፉት 18 ዓመታት አባላቶቹን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራው ባለው ስራ እንደ ሀገር ኅብረት ስራ ማህበራት በኢኮኖሚው እድገት ላይ ከፋተኛ አስተዋፆ እያበረከቱ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

አክለዉም አዋጭ የአባላት የገና ባዛርን ሲያዘጋጅ ያለምንም ክፍያ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ አባላቱን ለማገዝ እና ለማበረታታት አልሞ መሆኑን ገልፀው በዚህም  ፍቃደኛ የሆኑ ከ70 በላይ አባላት መሳተፋቸውን ተናግረዋል።

የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ሥላሴ አዋጭ ሾላ ገበያ ላይ በገዛው የግል ይዞታው  ይህን የአባላት የገና ባዛር በነፃ ማዘጋጀቱ አባላቶቹ ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለሸማቹ ማህበረሰብ እንዲያቀርቡ ከማስቻል ባለፈ ኅብረት ስራ ማህበሩ ወደፊት ሊሰራ ያቀደውን  ስራ በትንሹ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአራዳ ዲስትሪክት ዲጅታል ማናጀር የሆኑት አቶ አሸናፊ ተገኝ አዋጭ ኀብረተሰቡን ለማገዝ እየሰራ ካለው ስራ አኳያ የአባላት የገና ባዛርን በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር በማድረጋችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ያሉ ሲሆን ወደፊትም አብረን እንሰራለን በማለት ቃል ገብተዋል።
167410cookie-checkአዋጭ የአባላት የገና ባዛር ማዘጋጀቱን አስታወቀየአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በንግዱ …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE