በዛሬው እለት ብቻ ሦስት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል#Ethiopia | በሁለት ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ…

Reading Time: < 1 minute
*
በዛሬው እለት ብቻ ሦስት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል

#Ethiopia | በሁለት ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደሰባት ያህል የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸውን ቮልካኖ ዲስከቨሪ ገለፀ፡፡

ከእነዚህ መካከል አንደኛው ከመተሀራ ከተላ በሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ሲሆን የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በሬክተር ስኬል አራት ነጥብ ዘጠኝ መሆኑን መዝግቦታል፡፡ ሌላኛው መንቀጥቀጥ ደግሞ ከአዋሽ በሀምሳ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ መሆኑን የገለፀው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ይህኛው በሬክተር ስኬል አራት ነጥብ አራት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከእነዚህ ሁለት መንቀጥቀጦች ጥቂት ሰአታት ቀደም ብሎ በአፋር ክልል አዋሽ አቅራቢያ መጠኑ አራት ነጥብ ሰባት የሆነ ሌላ መንቀጥቀጥ መከሰቱን የጀርመን ጂኦ ሳይንስ ጥናት ማእከል ገልጿል፡፡ እንደቮልካኖ ዲስከቨሪ ዘገባ በሁለት ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጦች የተፈጠሩ መሆናቸውን የተለያዩ የጂኦ ሳይንስ ማእከላት አስታውቀዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል በሀረሪ ክልል የተፈጠረው ይገኝበታል፡፡ የእነዚህ መንቀጥቀጦች ስሜት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ንዝረት መፍጠራቸውም ተዘግቧል፡፡
167040cookie-checkበዛሬው እለት ብቻ ሦስት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል#Ethiopia | በሁለት ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE