የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መቄዶንያ የሚገኙ አረጋውያንን ጎበኙ ወጣቱ ባለጸጋም የኘሬዝዳንቱን ጉብ…

Reading Time: < 1 minute
*
የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መቄዶንያ የሚገኙ አረጋውያንን ጎበኙ

👉ወጣቱ ባለጸጋም የኘሬዝዳንቱን ጉብኝት በማስመልከት 8ሺ ለሚደርሱ አረጋውያንን 2 ሚሊየን ብር በመመደብ የምሳ ግብዣ አካሄዷል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ አዲስ አበባ የሚገኘውን መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን በዛሬው ዕለት በግቢው ተገኝተው ጉብኝት ያረጉ ሲሆን በዕየ ዓመቱ ታህሳስ 18 በእሳቸው ስም እንዲሰየም እና የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ የቀረበላቸውን ጥያቄም ተቀብለዋል።

“መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የሚሰራው በጎ ስራ ነውና፤ ሁሉም በአቅሙ ሊደግፈው ይገባል ያሉት ፕሬዚዳንቱ በመቄዶንያ እየተሰራ ያለው በጎ ስራ ብርታትን የሚሰጥ ነው ማዕከሉ የበጎ አድራጎት ሥራውን ይበልጥ ተደራሽ እንዲያደርግ ሁሉም በሚችለው ድጋፍ ማድረግ አለበት” ብለዋል።

ከእዚህ ጋር ተያይዞ የመቄዶንያ የምንግዜም አጋዡ ወጣቱ ባለጸጋ ምህረትአብ ሙሉጌታ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማውጣት የፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴን ጉብኝት ምክንያት በማድረግ በድርጅቱ ለሚገኙ 8 ሺ ለሚደርሱ አረጋውያን የምሳ ወጪ ሸፍኗል።

ለእዚህ በጎ ተግባሩ የመቄዶንያ መሥራቹ ዶ/ር ቢኒያም በለጠ ወጣት ምረትአብ ሙሉጌታ ለድርጅታችን እያደረገ ያለው ነገር ቀላል የሚባል አይደለም ዛሬም ሙሉ የምሳ ወጪ ስለሸፈነልን ከልብ እናመሠግናለን ብለዋል።

መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በ44 ከተሞች ከ8 ሺህ በላይ አረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማንን እየደገፈ ያለ ሲሆን፤ በቀጣይ ይህን ቁጥር ወደ 20 ሺህ ለማድረስ እየሰራ ይገኛል።
167020cookie-checkየኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መቄዶንያ የሚገኙ አረጋውያንን ጎበኙ ወጣቱ ባለጸጋም የኘሬዝዳንቱን ጉብ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE