“ስለ ነገ ” የአብርሆት የጥበባት ማዕድ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት በየወሩ …

Reading Time: < 1 minute
*
“ስለ ነገ ” የአብርሆት የጥበባት ማዕድ

በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው “ስለ ነገ” የአብርሆት የጥበባት ማዕድ መድረክ ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ሙዚየም በተከናወነ መርሃ – ግብር በይፋ ተከፈተ።

“ስለነገ ” የአብርሆት የጥበባት ማዕድ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ይዘት ያላቸው ስራዎች በየወሩ ለህዝብ የሚቀርብበት መድረክ ሲሆን ኀብረተሰብ በሚዘጋጁ የኪነጥበብ መድረኮች ላይ እንዲታደም ጥሪ ቀርቧል።

የመርሐግብሩን ይዘት አስመልክቶ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) እንደገለጹት “የምናካሂደው ስለ ነገ አብርሆት የጥበባት ማእድ መድረክ እንደ ሀገር ኢትዮጵያዊነታችን ፣ የጋራ የወል ትርክቶች የህዝባችን አንድነትና መልካም ገፅታ በኪነ-ጥበብ አማካኝነት ለቀጣይ ትውልድ የምናስተላልፍበት መድረክ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት ምክረ ሀሳብ “በኪነ ጥበብ ዝግጅቱ ተሰጥኦአቸውን ያቀረቡ ታዳጊዎች በየሰፈሩ ዕድሉን ካገኙ ብዙ መስራት የሚችሉ መኖራቸውን ማሳያ ናቸው ብለዋል።

“ስለ ነገ” በአብረሆት ጥበባት ማዕድ ላይ ታዋቂ ገጣሚያን ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ፣ የተለያዩ ህብር ዜማዎች ፣ የዳንስ ቀርበዋል ዝግጅት ቀርበዋል ። በመርሐ – ግብሩ ላይ
የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ አባ ገዳዎች ፣ አንጋፋ እና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።
166870cookie-check“ስለ ነገ ” የአብርሆት የጥበባት ማዕድ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት በየወሩ …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE