ዘመናዊው 50 ሚሊየን ብር የሚያወጣው የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ስክሪን ተመረቀ
📌 ስክሪኑ 8K ቪዲዮ ጥራት ድረስ ማጫወት እንደሚችል ተጠቅሟል።
50 ሚሊየን ብር የሚያወጣው ስክሪን ተመረቀ:: በኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት (EOTC TV) አዲሱ ስቲዲዮ ተመረቋል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ እውቅና የተሰጠው “ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር “ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
በምረቃው መርሐግብር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
አንድ ዘመናዊ ስቱዲዮ ማሟላት የሚገባው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ግዙፍ 8k ስክሪን የተገጠመለት እና የተለያዩ ቀረጻዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ገጽታዎች እና የግንኙነት ካሜራ የተገጠመለት የስቱዲዮ መቆጣጠሪያ ክፍል ያለው ሲሆን ግንባታው ባለፉት ከ3 ዓመታት በላይ መውሰዱ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መስራች መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ሙሉ ወጪ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ ድርጅቱ በሚያሠራጫቸው ይዘቶች የፕሮዳክሽን ጥራት ለመጨመር ከፍተኛ አስተውጽኦ እንደሚያመጣ ተገልጿል።
የቴሌቪዥን ተቋሙ በቅርቡ ከሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ኅብረት በተደረገለት ድጋፍ የቀጥታ ሥርጭት የጀመረ ሲሆን በሣተላይት በኢትዮ ሳት እና በዲኤስ ቲቪ እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ ሥርጭቱን ይበልጥ በማሳደግ ላይ ይገኛል።
የተገጠመለት የስክሪኑ አይነት P1.5 LED indoor screen (GOB) Glue on board የሚባለው ሲሆን ይሄም ቴክኖሎጂ ለስክሪኑ ከሚሰጠው ጥቅሞች መካከል
📌 ላምፖቹ ፕሮቴክቲቭ እንዲሆኑ ይረዳል
📌 ያለ ምንም ብልሽት እስክሪኑ ለረጅም ጊዜ እንዲሰራ ይረዳዋል
📌 ሳውንድና ደስት ፕሩፍ ነው
📌 በቀላሉ ማፅዳት ይቻላል
📌 እስሪኑ ማግኔቲክና front maintenance ነው
📌 Processor
7 input ያለውና በአንድ ጊዜ 3እና ከዛ በላይ out put ያለው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ፍኖተ ፅድቅ በዚህ አመት ብቻ ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ጨምሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች 739 ሚሊየን 810ሺ ብር ማዋሉም ታውቋል።