ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ከ9200 በላይ ተማሪዎችን ለ22ኛ ጊዜ አስመረቀ። ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበ…

Reading Time: < 1 minute
*
ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ከ9200 በላይ ተማሪዎችን ለ22ኛ ጊዜ አስመረቀ።

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች በሚገኙ 18 ካምፓሶች በተለያየ የትምህርት አይነቶች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አስመረቀ።

የዩኒቨርስቲው መስራች እና ባለቤት አቶ ዱንቁ ደያስ በተማሪዎች ምረቃ መርሐግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ለተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኃላ ከ24 ዓመታት በፊት፣ “ሕዝቤ ይማር” በሚል ራእይ በመነሳት ከትንሽ መዋዕለ ህፃናት የጀመረው ትውልድን የማነፅ ሥራ የህዝባችን ድጋፍ ተጨምሮበት ለዚህ ደረጃ በመብቃቱ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ያሉ ሲሆን በቀጣይ የተጀመረው የትምህርት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አቶ ዱንቁ ደያስ ጨምረው እንደገለጹት በተለይ በመምህራን ልማት በኩል መልካም ሥራ እንደተሰራ የገለጹ ሲሆን በርካታ መምህራን በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት በሀገር ውስጥ እንዲማሩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ላይ ተደርሶ ብዙ መምህራን በመማር ላይ ሲሆን በርካቶችም ትምህርታችዉን በመከታተል ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በዛሬው እለት የተመረቁት ተማሪዎችም በ18 ካምፓሶቹ በተለያዩ የሙያ ዘርፎችና መስኮች ማለትም በጤና በቢዝነስና በማህበራዊ ሳይንስና በቴከኖሎጅ ፋካልትዎች በተለያዩ ደረጀዎች በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ከ9200 በላይ ተማሪዎች ናቸው።

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ በጤና ፣ በቢዝነስና በማህበራዊ ሳይንስ ፣በቴክኖሎጂ ፋካልትዎች በተለያዩ ደረጃዎች በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በመስጠትና በርካታ ተማሪዎችን በማስመረቅ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል።
147130cookie-checkሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ከ9200 በላይ ተማሪዎችን ለ22ኛ ጊዜ አስመረቀ። ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE