በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት “የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና!” በሚል መጠሪያ መንፈሳዊ ፣ ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት

Reading Time: 2 minutes
*

“የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና”!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት “የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና!” በሚል መጠሪያ መንፈሳዊ ፣ ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ላይ ትኩረቱን ያደረገ እና ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 30 ቀን2016 ዓም ድረስ የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ትግብር መግባቱን  ይፋ አደረገ።

ኘሮጀክቱን ይፋ መደረጉን አስመልክቶ ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት  ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አካባቢው ጠረፋማ ከመሆኑ የተነሳ ትኩረት የሚሻ አካባቢ ከመሆነም በላይ ከሌሎች የአገራችን ክፍሎች አንጻር ከስልጣኔ እና ከእድገት ወደኋላ የቀረ ቢሆንም በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች ለም የሆነ መሬት እና መልካም አጋጣሚዎች ያሉ በመሆኑ  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረስብከት ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማስፋት በተጨማሪ ምዕመኑን ተጠቃሚ የሚያደርግና የዞኖቹን የልማት ሥራዎች የሚደግፍ ፕሮጀክቶች ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ብጽኡነታቸወ ገልጸዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያው ፕሮጀክት ከተካተቱት መካከል፥
የ100 ብር፣ 250 ብር፣ 500 እና 1,000 ብር ዋጋ ያላቸው አንድ መቶ ሺ ትኬቶችን በአዲስ አበባ በሚገኙ ገዳማት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ ማህበራትና የንግድ ተቋማት በኩል በማሰራጨት ምዕመናን እንደ አቅማቸው ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል ተብላል።

የክፍያ መተግበሪያ አማራጮችን በመጠቀም የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችንና የአሐዱ ባንክ የድጋፍ መለገሻ መተግበሪያን (Donation App) ጭምር በመጠቀም በርካቶች ባሉበት ሆነው E-ticket በመግዛት ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ ከሐምሌ 15 ቀን  ጀምሮ ክፍት የሚሆን ሲሆን በበይነ መረብ ማሰባሰቢያ መንገድ ተደራሽ መሆናል።
ሐምሌ 27 እና 28 2016 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሰላም መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን የሀገረ ስብከቱን ታሪክ፣ የስብከተ ወንጌልና የልማት ስራዎችን የሚያስቃኝና የልማት ውጤቶችንና ሥራዎች ለገበያ የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ የሚካሄድ ሲሆን ሐምሌ 28 ማታ ብጹዓን አባቶች፣ ሰባክያነ ወንጌሎችና ዘማሪያን የሚሳተፉበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቤተክርስቲያኑ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ከዚህም ባሻገር በነሐሴ ወር መጨረሻ ብጽዐን አባቶች፣ የሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና የአድባራት ደብር አስተዳዳሪዎች፣  ባለሀብቶች፣ የንግድ ተቋማት የሚሳተፉበት የእራት መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

የደቡብ ኦሞና የአሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ከአዲስ አበባ 735 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ በጅንካ ከተማ ላይ ይገኛል፡፡ በሃገረ ስብከቱ በተከናወነ ከፍተኛ የወንጌል አገልግሎት ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት ብቻ ከ185, 000 (አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ) በላይ ምዕመናን ተጠምቀው የሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን ያስተባባረው ሎዛ ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ ነው።
146790cookie-checkበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት “የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና!” በሚል መጠሪያ መንፈሳዊ ፣ ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE