“ቴኳንዶ ለሁሉም” የተሰኘ መጽሐፍ በይፋ ተመረቀ!በግሎባል ማስተር አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል አማካኝነት የተ…

Reading Time: < 1 minute
*
“ቴኳንዶ ለሁሉም” የተሰኘ መጽሐፍ በይፋ ተመረቀ!

በግሎባል ማስተር አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል አማካኝነት የተጻፈው “ቴኳንዶ ለሁሉም” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ በትናንትናው እለት በካፒታል ሆቴል በርካታ የጽሐፊው የሙያ አጋሮች ፣ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

“ቴኳንዶ ለሁሉም ” መጽሐፍ በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ላይ ያሉ ዋና ዋና መርሆች ማለትም ከቴኳንዶ ዓለማቀፍ እስከ አገር አቀፍ ታሪክ ጀምሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች፣ ራስን የመከላከል ጥበቦች ፣ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ እስከ ጥቁር ቀበቶ (አንደኛ ዲግሪ) ድረስ ያሉ ፑምሴ (አርት) ሁሉም መሰረታዊ እንቅስቃሴዎችን እና የቴኳንዶ ስነ-ምግባርና ፍልስፍና አጠቃሎ የያዘ እንዲሁም የሰልጠና ማኑአል ፣ የመወዳደሪያ ህጎችና ፣ የቀበቶ ደረጃ አሰጣጥን እንደ ማስተማሪያም ሊያገለግል በሚችል መልኩ በግሎባል ማስተር አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል አማካኝነት የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው፡፡

መጽሐፉ ከአማርኛ ቋንቋ ባሻገር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቅርቡ ለአንባቢያን የሚደርስ መሆኑን ግሎባል ማስተር አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል በምረቃው መርሐግብር ላይ ለተገኙ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ገልጿል።
146750cookie-check“ቴኳንዶ ለሁሉም” የተሰኘ መጽሐፍ በይፋ ተመረቀ!በግሎባል ማስተር አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል አማካኝነት የተ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE