“ዘመን ተዋህዶ ኤክስፖ” በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ተከፈተ።
ማርኮናል እና ሎዛ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ ይህ ኤክስፖ ዛሬ ሀምሌ 12/2016 ዓ / ም በኤግዚቢሽን ማእከል መክፈቻው ተከናውኗል።
በባለፈዉ ገና በአል ሊዘጋጅ ታቅዶ የነበረዉ ገና ተዋህዶ ኤክስፖ አጋጥመዉ በነበሩ ችግሮች ምክንያት መቅረቱን ያስታወሱት አዘጋጆቹ ይሄኛዉ ኤክስፖ ለአዲሱ አመት መዳረሻ መሆኑን ገልፀዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀዉ ዘመን ተዋህዶ ኤክስፖ ከ ዛሬ ሀምሌ 12 እስከ ሀምሌ 21 የሚቆይ እንደሆነ ታዉቋል።
700 ያህል ነጋዴዎች ፣ አስመጪዎች ፣ አካፋፋዮች ፣ የንግድ ተቋማት የሚሳተፉበት እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን አምስት ሺህ ያህል ጎብኝዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በአዘጋጆቹ ተገልጿል።
ከኤክስፖዉ የሚገኘዉ ገቢ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ገዳማት እና ቤተክርስቲያኞች የሚዉል በመሆኑ በቀጣዩቹ ቀናት ህብረተሰቡ የሚሳተፍበት እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
የዘመን ተዋህዶ ኤክስፖ የመግቢያ ዋጋ 50 ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በኤክስፖዉ መሳተፍ የሚፈልግ የንግዱ ማህበረሰብ በቦታው ተገኝቶ ግብይት ማድረግ የሚችል መሆኑ ታወቋል።
በቀጣይ ጊዜያት ሀገራዊ እና ሀይማኖታዊ በአላትን ምክንያት አድርጎ ከአዲስአበባ ዉጪ ባሉ ክልል ከተሞች ላይ መሰል መርሀግብሮችን የማዘጋጀት እቅድ መያዙን ለማወቅ ተችሏል።