በጅማ አከባቢ ተሰማ የተባለው ከፍተኛ ድምጽ ከጠፈር በወደቀ ድንጋይ መሰል ቁስ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር…

Reading Time: < 1 minute
*
በጅማ አከባቢ ተሰማ የተባለው ከፍተኛ ድምጽ ከጠፈር በወደቀ ድንጋይ መሰል ቁስ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ተጠቆመ።

ከትናንት በስቲያ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከፍተኛ ድምጽ መሰማቱንና በማኅበራዊ ሚዲያም መሬት ላይ ወድቆ ተገኘ የተባለ ድንጋይ መሰል ቁስ በስፋት ሲዘዋወር ነበር።

በዚህ ዙሪያ #ኢትዮጵያቼክ በጠፈር ሳይንስ እና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የአስትሮፊዚክስ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑትን ዶ/ር ሰለሞን በላይን አነጋግሮ ነበር።

ዶ/ር ሰለሞን “ከተመለከትኳቸው ምስሎች መረዳት የቻልኩት ወደቁ የተባሉት አካላት የሚቲዮራይት ስብርባሪ መሆናቸውን ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ዲፓርትመንትን በዚህ ዙርያ እንዳናገሩና ተመሳሳይ ምላሽ እንዳገኙም ነው የገለጹት። ወድቆ የተገኘው አካል ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ ለምርመራ እንደሚወሰድም ተናግረዋል።

ለመሆኑ ሚቲዮራይት እንዲሁም ሜቶር፣ ሜትሮይድ አስትሮይድ የምንላቸው ምንድን ናቸው?

አስትሮይድ (Asteroid) የምንለው በሥርዓተ ፀሐያችን ውስጥ የተፈጠሩና ልክ እንደ ፕላኔቶች ፀሐይን የሚዞሩ ፍጥረተ ቅሪት ናቸው። በርካታ አስትሮይዶች በሕዋ ሥርዓታችን ውስጥ ይገኛሉ

ሜትሮሮይድ ከኮሜት፣ ከአስትሮይድ፣ እንዲሁም አንዳንዶቹ ከጨረቃ እና ከሌሎች ፕላኔቶች በፍንዳታ እና በሌሎች የመጡ ምክንያቶች ሊሸራረፍ ይችላል።
146230cookie-checkበጅማ አከባቢ ተሰማ የተባለው ከፍተኛ ድምጽ ከጠፈር በወደቀ ድንጋይ መሰል ቁስ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE