ሆራ ትሬዲንግ እና ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ ተፈራረሙ !!ሆራ ትሬዲንግ እና ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አዳዲስ የ…

Reading Time: < 1 minute
*
ሆራ ትሬዲንግ እና ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ ተፈራረሙ !!

ሆራ ትሬዲንግ እና ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በተመጣጣኝ ዋጋና በተመቻቸ የአከፋፈል ሁኔታ ለማኅበረሰቡ በብድር ለሽያጭ ለማቅረብ ተስማሙ ።

ሁለቱ ተቋማት ዛሬ የተፈራረሙት BYD ኤሌክትሪክ መኪና ከ40 እስከ 50% በመቶ ቅድመ ክፍያ ተጠቃሚዎች የመኪና ባለቤት ማድረግ የሚችሉበትን አሰራር ለመፈጥር ነው።

የመኪና ገዢዎችም ከላይ የተጠቀሱትን ቅደመ ክፍያዎች በአንድ ጊዜ ወይም በአራት ወራት ውስጥ በሚያደርጉት ቁጠባ መሰረት የመኪና ባለቤት መሆን የሚቻሉበትን ዕድል ይፈጥራል።
የመኪና ገዢዎች ቅድመ ክፍያቸውን እንዳጠናቀቁ እና መኪናቸውን ከተረከቡበት ጊዜ አንስቶ በአምስት አመታት ውስጥ ክፍያቸውን እንዲያጠናቅቁ ሁኔታዎች ይመቻችላቸዋል።

በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ የቡና ግብይት ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላቸው አንጋፋ የቡና ነጋዴ በሆኑት አቶ አደም ከድር የተመሰረተው ሆራ ትሬዲንግ በ2005 ዓ. ም በኢትዮጵያ የተመሰረተ ዘርፈ ብዙብየግል ኩባንያ ነው ።
በዋናነት በወጪና ገቢ ንግድ ስራ ተሰማርቶ ይገኛል ። ከጥቂት ጊዜ በኃላ ሆራ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ግሩፕ ወደ ሚባል ልዩ ልዩ ይዞታ ኩባንያ አድጓል ።
145500cookie-checkሆራ ትሬዲንግ እና ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ ተፈራረሙ !!ሆራ ትሬዲንግ እና ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አዳዲስ የ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE