ኢትዮ አውቶሞቲቭ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ኤክስፖ ተከፈተ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮ…

Reading Time: < 1 minute
*
ኢትዮ አውቶሞቲቭ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ኤክስፖ ተከፈተ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮ አውቶቴክ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ኢትዮ አውቶሞቲቭ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኤክስፖ በዛሬው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ በይፋ ተከፈተ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በአውደ ርዕዩን መክፈቻ መርሐግብር ላይ ተገኝተው እንደገለጹተ “የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው በሚፈለገው ደረጃ ባለመደራጀቱና ትኩረት ተሰጥቶ ባለመሰራቱ ሌሎች ሀገራት ከዘርፉ የሚያገኙትን ጥቅም በሚፈለገው ደረጃ ሳይገኝ ቆይቷል” ያሉ ሲሆን “ባለፉት አራት ዓመታት መንግስት ተግባራዊ ያደረጋቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ባስገኙት ዕድሎች ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ካሉት ታላላቅ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች አንዱ በመሆን በሀገራችን ብሔራዊ ልማት ውስጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን” ገልጸዋል፡፡

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ላይ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ፤ በትራንስፖርት ምርት፣ ጥገና እና ሽያጭ የተሰማሩ ተቋማት ጨምሮ ባለድርሻ አካላትን የሚሳተፉበት ሲሆን ግለሰቦች እና ተቋማት የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለጎቢኚዎች የሚያስተዋውቁ ይሆናል።

ከኤክስፖው ጎን ለጎን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር የተካሄደ ሲሆን ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት ሁኔታዎችን መፍጠር ላይም ውይይት ተካሄዷል።
143930cookie-checkኢትዮ አውቶሞቲቭ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ኤክስፖ ተከፈተ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE