የሁለገቡ ከያኒ ነቢይ መኮንን የቀብር ሥነሥርዓት ነገ በናዝሬት ይፈጸማል
• በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ የስንብት መርሃ ግብር ይካሄዳል
በናዝሬት- አዳማ አፈር ፈጭቶ ያደገውና ፊደል ቆጥሮ የተማረው አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ነቢይ መኮንን፣ በህይወቱ ፍጻሜ ላይ ለዘላለም ሊያርፍበት የመረጠው ቤት የእናቱን ነው ተብሏል፡፡
ቤተሰቦቹ እንደገለጹት፣ ነቢይ መኮንን ዛሬ ማለዳ ለዘላለም ከማሸለቡ በፊት በተናገረው የመጨረሻ ቃሉ፤ “በምወዳት ከተማዬ ናዝሬት፣ ከምወዳት እናቴ ማረፊያ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ቅበሩኝ” ብሏል፡፡
በዚሁ መሰረት፣ የሁለገቡ ከያኒ ነቢይ መኮንን የቀብር ሥነስርዓት፣ ነገ ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9 ሰዓት፣ በአዳማ/ናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡
ከዚያ አስቀድሞ ግን በነገው ዕለት ሐሙስ ከረፋዱ 3፡30 – 4 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ፣ አንጋፋ የኪነጥበብ ሙያ አጋሮቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል፡፡