”መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ”መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“ በሚል መሪ ሀሳ…

Reading Time: < 1 minute
*
”መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ”መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“ በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው ለሁለት ወራት የሚቆይ የንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በይፋ ተጀመረ።

በንቅናቄ መድረኩ ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እንደገለጹት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ብሎም በመጡበት ፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ በማሰብ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የሊዝ ቅድመ ክፍያ ከ10 በመቶ ወደ 5 በመቶ እንዲሁም የሼድ ኪራይን በፊት ከነበረበት የ 10 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ ሪፎርሞች ተግባራዊ መደረጋቸው ባለሀብቶቹ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ በዚህም ካለፈው ሁለት ዓመት ወዲህ ከ60 በላይ ሀገር በቀል ባለሃብቶች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል፡፡

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከነበረው ንቅናቄ መድረኩ ማስጀመሪያ መርሐግብር ባሻገር በቂሊንጦ በነበረው የጉብኝት መርሐግብር ላይ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ሶሊሰብ ሜዲካል አምራች እና ሄሊንግ ግሎቭ የተሰኙ ሁለት ተቋማት ጋር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዛሬው እለት በነበረው በንቅናቄ መድረኩ ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ከ70 በላይ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ተሳትፈዋል።
141690cookie-check”መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ”መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“ በሚል መሪ ሀሳ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE