ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት  በብድር አስረከበ።…

Reading Time: < 1 minute
*
ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት  በብድር አስረከበ።

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች በበርካታ ሃገራት ተመራጭነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ይገኛል ኢትዮጵያም እንደ ሃገር የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ብሎም የአየር ንብረትን ለመጠበቅ ይረዳ ዘንድ የኤሌክትሪክ መኪናን እንደ አማራጭ የመጠቀም ፓሊሲን ከመተግበር ባለፈ በሃገራችን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል።

ይህንን ፖሊሲ እና የተጠቃሚዎች ፍላጎት ከግምት በማስገባት የአለማችን ተጠቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የሆነው የ”ሆን ዞ” አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ለተጠቃሚዎች እያቀረበ ይገኛል።

የዜጎችን ኑሮ ባማከለ መልኩ በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት እነዚህ የኤሌክት መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና ያላቸውም ናቸው።

ለዚህም በዛሬው ዕለት ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮፒካር ብራንድ ከግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም ጋር የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለተቋሙ አባላት በብድር መስጠት የሚያስችል ስምምነት ፈፅሟል፡፡
 
በዚህ ስምምነት መሰረትም የ”ሆን ዞ” አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት የሚፈልጓቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ምቹ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ በብድር  እንደሚሰጥ ”የኢቲዮፒካር” ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አዲስአለም  ገልፀዋል።

በተጨማሪም ዛሬ ግንቦት 29/2016 ዓም  ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት ለሆኑና የብድር መስፈርቱን አሟልተው 30 በመቶ ቁጠባ ለፈፀሙ አባላት የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል።
140090cookie-checkኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት  በብድር አስረከበ።…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE