ሆቴል ላልሆነ በሆቴል ኢንቨስትመንት ስም ቦታ ሊተላለፍ ነው!!
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንበል አደባባይ አካባቢ ” ጄኔቭ የመኪና አስመጪና ሻጭ ድርጅት ” የተከራየው ህንፃ የኪራይ ውሉ እንዲቋረጥ ሊደረግ በመሆኑ ያለውን ቅሬታ እያቀረበ ይገኛል።
የጀኔቭ ዋና እና ምክትል ማናጀሮች ቅሬታቸው ፦ ህንፃው ለMixed አገልግሎት ሆኖ ሳለ ለሆቴል ማስፋፊያ ይሰጥ መባሉ፣
-እኛ እራሳችን ከፍተኛ ግብር ከፋይ ሆነን ለሌላ ለሆነ አካል ይሰጥ መባሉ፣
– ቤቱ ለልማት ይሰጥ ተብሎ የካቢኔ ውሳኔ ባለማግኘታቸው፣
– ለልማት ይሰጥ የተባለው በ2013 ዓ/ም ሆኖ ሳለ አሁን ውሉ ይቋረጥ መባሉ፣
– ቤቶች ኮርፖሬሽን ሊሟገት ሰገባው የኪራይ ውሉ እንዲቋረጥ የድጋፍ ደብዳቤ በመፃፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ራሱ ኮርፖሬሽኑ ቢያለማው እኛ መልቀቅ እንችላለን የመንግስት ቦታ ስለሆነ ግን ለምንድነው ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ የሚሰጠው ? ያውም ሆቴል ሳይሆን ሆቴል ተብሎ ሲሉ ጠይቀዋል።
የቤቶች ኮርፖሬሽን የፃፈው የድጋፍ ደብዳቤ ላይ፥ ምክንያቶቹን በዝርዝር ካብራራ በኋላ፣ የተከራይ ውል እንዲቋረጥ ያዛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ኮርፖሬሽኑን ጠይቋል።
የኮርፖሬሽኑ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አማኑኤል አያሌው፣ “ የመጀመሪያ ስህተቱ ሰዎቹ ልክ እንደ ግል ይዞታ አድርገው እያቀረቡ ነው። ይዞታው የቤቶች ኮርፖሬሽን ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ ደግሞ የንግድ ቤት ተከራይ ናቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ከተማ አስተዳደሩ ‘እዚያ አካባቢ የሆቴል ዲዛይን ነው’ አለ። እኛ ሆቴል አንገነባም። ስለዚህ እኛ ይዞታ አናስተላልፍም ለግለሰብ። እሳቸውም ለእኛ ቅሬታ ቢያቀርቡ መስጠት አንችልም ” ብለዋል።
አቶ አማኑኤል፣ “ ቅሬታ ካላቸው ለከተማ አስተዳደሩ ነው ማቅረብ ያለባቸው። ቦታው ለእኔ ይመደብ ብለው ማቅረብ ይችላሉ ” ነው ያሉት።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ቦታው ለልማት እንዲነሳ በካቢኔ ስለመወሰኑ እንደማያውቁ ላነሱት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ አቶ አማኑኤል፣ “ የካቢኔ ውሳኔ ተለጥፏል ያውቃሉ። በ2013 ዓ/ም የተለጠፈ የካቢኔ ውሳኔ ነው ” ብለዋል። (ይህን የሚገልጽ ዶክመትም አሳይተዋል)
ለቲክቫህ የላኩት ሰነድም ህንፃው ለልማት እንዲነሳ በከተማ አስተዳደሩ በ2013 ዓ/ም መወሰኑን ያትታል።
እንዲሁም፣ ቦታው ለMixed አገልግሎት ሆኖ ሳለ ለምን ለሆቴል ማስፋፊያ ይሰጥ በመባሉ ጀኔቭ ላነሳው ቅሬታ፣ “ ይህ ሰው ተከራይ ነው። ይህን ያህል ቅሬታ ማንሳት የለበትም፣ ተቀባይነት የለውም ” ብሏል ኮርፖሬሽኑ።
“ ተከራይ ነው፤ በንግድ ህጉ መሠረት ይህ ሰው ሲዋዋል መንግስት ወይም ኮርፓሬሽኑ ቤቱን ለልማት ሲፈልገው ውል ያቋርጣል ይላል ” ነው ያለው።
ተወሰነ የተባለው በ2013 ዓ.ም ሆኖ ሳለ ለምን አዘግይቶ አሁን መጠየቅ አስፈለገ ? ሲል ጀኔቭ ላነሳው ጥያቄ አቶ አማኑኤል፣ “ አብዛኛውን ውሳኔ አንቀበልም። መሬቱን ማቆየትና ማልማት ስለምንፈልግ ” ሲሉ መልሰዋል።
አክለው፣ “ ግን አሁን የአዲስ አበባ ከተማ መልሶ ማልማት ላይ ያለው ‘ ከመንግሥት እንቅፋት እየሆነናችሁ ነው ’ የሚል ቅሬታም እየመጣ ስለሆነ ማልማት በምንችለው መንገድ እኛ እናለማን። ባለሃብቱ ማልማት ባለበት ደግሞ ባለሃብቱ ” ነው ያሉት።
የጄኔቭ ማናጀር አቶ አብርሃም ለማ በበኩላቸው፣ “ ራሳቸው ተጠይቀው የሰጡት መልስ አለ። ‘ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መካከል አንዱ ጄኔቬ የመኪና አስመጪ ሲሆን ራሱን ችሎ የሚገነባ ቦታ ስለሆነ ራሳችን እንገነባለን። ካልሆነ ደግሞ ተከራዩ ማልማት የሚችል ከሆነ ቅድሚያ እንሰጣለን’ ” የሚል ምላሽ ከከተማ ከንቲባ ለቀረበላቸው ጥያቄ እንደሰጡ ተናግረዋል።
via ቲክቫ – ኢትዮጵያ