የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ልዮ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመ…

Reading Time: < 1 minute
*
የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ልዮ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመልከቱ ! ንፁህ አየር ይተንፍሱ !» በሚል መሪ ቃል ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ውስጥ ልዮ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ሁለት ቀናት በሚቆየው መርሐግብር ላይ የአዋቂዎች የተራራ ላይ የእግር ጉዞ፣ አዝናኝ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የህፃናት መዝናኛ መጫዎቻዎች፣ የፈረስ እና ግመል ግልቢያ ፣ የማዕከሉ ሳቢና ማራኪ መልክአ-ምድራዊ አቀማመጥ ጉብኝት ፣ የመፅሀፍ ዓውደ-ርዕይ እንዲሁም የተለያየ የዕደ-ጥበብ ስራዎች በተግባር የሚሞከሩበት
መሠናዶዎች ያለምንም የመግቢያ ክፍያ በነጻ እንደተዘጋጁ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የደንበኛች ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ክንፈ ገብረማርያም ገልጸዋል።

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን እነዚህ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ክንፈ ገብረማርያም ጨምረው ገልጸዋል።

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ705 ሄክታር ቦታ ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ይገኛል። የዕፅዋት ማዕከሉ ከባህር ጠለል ከ2600- 2950 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ950 በላይ ሀገር በቀል የዕፅዋት ዝርያዎችን ይዟል።
135550cookie-checkየጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ልዮ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE