አምስት መቶ በላይ ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጀመረ።
በውድድሩ አሸናፊዎች አንድ ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከሳኦል ኩነቶች አዘጋጅ ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ግዙፉ እና በአይነቱ ልዩ የሆነው የ2016 የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ኦፕን ቶርናመንት ከግንቦት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በትልቁ ጅምናዚየም ተጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኋላፊ አቶ ጥላሁን ዋሲሁን የስፖርት ውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ እንደገለጹት በቴኳንዶ ስፖርት ላይ ያሉ ተወዳዳሪዎችን ለማነቃቃት፣ ልምድ እንዲቀስሙ፣ በተወዳዳሪዎች ዘንድ የፉክክር መንፈስ እንዲኖር ፣ ክለባቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ሀገርን የሚወክሉ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለማግኘት ይረዳል ብለዋል።
አቶ ጥላሁን አያይዘውም ይህ ውድድር የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ግብ መጥቶልናል፤ ያሰብነው ተሳክቷል። ለአሸናፊዎችም ከሜዳልያ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት አዘጋጅተናል በማለት ተናግረዋል።
ውድድሩ የፊታችን ማክሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲሆን መታደም የሚፈልግ በሙሉ ጉለሌ መድኃኒያለም አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርት ስልጠና ማዕከል በትልቁ ጅምናዚየም በመገኘት መታደም ይቻላል ተብሏል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ አምባሳደሮች አርቲስቶች፤ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፤ባለሀብቶች፤ የስፖርቱ ባለሙያዎች እና አሰልጣኞች ተገኝተዋል።