ጥንታዊ ከተማ የሆነችው ሀረር ከተማ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ ቅርሶቿ በተጨማሪ በርካታ የቱሪስት መስቦች እንዳሏት ይነገራል፡፡ ካሏት መስቦች መካከል ደግሞ የጅብ ማበያ ስፋራ አንዱ ነው ፡፡
ይህ ስፋራ ከሀገር ውስጥ ቱሪስት ባሻገር በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎችም ሀረር ደርሰው የሚጎበኙት ስፋራ ነው፡፡
የጅብ ማብያ ስፋራው ለቱሪስቶች ምቹ ያልሆነ መሆኑን የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ስፋራው ለቱሪስቶች ምቹ ለማድረግ በሚል ተጨማሪ አዲስ የጅብ ማበያ ቦታ ሊገነባ መሆኑን የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ተወለዳ አብዶሽ ለመናኸሪያ ተናግረዋል፡፡
አሁን በሚገነባው የጅብ ማብያ ስፋራ ከዚህ ቀደም ከሚደረጉ ጅብ የማብላት ስራዎች በተጨማሪ ቱሪስቶችን የሚስቡ ሌሎች ስራዎች መሰራታቸውንም ገልፀዋል፡፡











