የራይድ አሽከርካሪውን ገለው መኪናውን ይዘው ተሰወሩሶፎንያስ አስራት ይባላል የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ…

Reading Time: < 1 minute
*
የራይድ አሽከርካሪውን ገለው መኪናውን ይዘው ተሰወሩ

ሶፎንያስ አስራት ይባላል የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ ለሊት 8 ላፍቶ አካባቢ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ኖሆም ሆቴል አካባቢ የሰፈሩ ስም ላፍቶ ቦሌ ሚካኤል ውሰደን ብለውት ጓደኞቹን ደርሼ መጣው ብሎ እንደወጣ በዛው ቀረ።

በማግስቱ እናቱ ስልኩ ላይ ስደውል አይሰራም ጓደኛው ጋር ስደውል ቦሌ ሚካኤል ብሎ እንደወጣ እና እንዳላገኘው ይነግራታል።

የፈለገ ነገር ቢፈጠር ከእናቱ ጋር ይደዋወል ነበር የልጇ ደብዛ መጥፋት ያስጨነቃት እናት ቦሌ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ትጠይቃለች የተመዘገበ ነገር ካለ እናሳውቅሻለን ይሏትና ተመልሳ ላፍቶ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ጠየቀች እነሱም ተመሳሳይ ነገር ነገሯት እና የአቃቂን ቃሊቲን ስልክ ይሰጧታል።

ስደውል ስልኩን ለሌላ ሰው ስጪ ብለው ያለውን ነገር ማለትም ወጣቱ መገደሉን እና አስክሬኑ ማሰልጠኛ አካባቢ እንደተገኘ እንዲሁም ለምርመራ ጳውሎስ እንደተወሰደ ይነግሯታል።

ዛሬ 5 ሠሀት አካባቢ አስክሬን ተቀብለው ወደ መኖርያ ቤት ወደ ላፍቶ ኮንደሚኒየም ወሰዱት ገዳዮቹ አልተገኙም መኪናውንም ይዘው መሠወራቸውን የሟች ሶፎንያስ የቅርብ ወዳጆች መረጃውን ለየኔታ ቲዩብ አድርሰዋል።

Via Yeneta tube
86790cookie-checkየራይድ አሽከርካሪውን ገለው መኪናውን ይዘው ተሰወሩሶፎንያስ አስራት ይባላል የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE