እናት ወተት ተዋናይት ራሄል እንግዳን በ2 ሚሊዮን ብር የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ።
ርሆቦት ኃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር የፊልም ተዋናይቷን አርቲስት ራሄል እንግዳን ብራዳችንን በማስተዋወቅ ጉልህ ሚና ትጫወታለች በማለት የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር በማደረግ ዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነ ፕሮግራም መርጧል።
ሮሆቦት ለብራንድ አምባሳደር አርቲስት ራሄል እንግዳ ሁለት ሚሊዮን ብር እንደከፈላት የተገለጸ ሲሆን ተቋም በስሩ እናት የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ፣ እናት የወተት ላሞች እርባታ እና እናት የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሶስት አንድ አላማ ያላቸው ተመጋጋቢ ፕሮጀክቶች የያዘ ግዙፍ ተቋም እንደሆነ የሮሆቦት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘበነ ታምሬ ተናግሯል።
ርሆቦት መጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ.ም በሁለት መስራች አባላት የተመሰረት ሲሆን በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር አረርቲ ከተማ በ1010 ሜትር ካሬ ላይ ያረፈ ማቀነባበሪ ፋብሪካ ነው።
በቀጣይ የትንሳኤ በአል ምክንያት በማድረግ በይዘቱ ልዩ የሆነ አስተሻሸግ ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል።