የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና እየሰጠ ነው።የአዲስ …

Reading Time: < 1 minute
የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና እየሰጠ ነው።

የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን፤ የ2016 ዓ.ም 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠናና ዓለማቀፍ የፕሮ ቴኳንዶ የመጀመሪያ ራስን መከላከል ኮርስ በወወክማ አዳራሽ ውስጥ እየሰጠ ነው።

ከመጋቢት 14 እስከ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ለ15 ቀናት ይዘልቃል በተባለው በዚህ ሥልጠና ላይ ከ35 በላይ ሰልጣኞች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ማስተር ሃይለየሱስ ፍስሃ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ ይኼ አሁን በመሰጠት ላይ የሚገኘው 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና፣ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሠጠው የመጀመሪያ ኮርስ ነው ብለዋል።

ሥልጠናውም በአምስት የሌጀንድ አሰልጣኞች፣ ከ35 በላይ ለሚሆኑ ከአዲስ አበባና የተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንደሚሰጥ የሌጀንድ ኢንተርናሽናል ማስተር ሃይለየሱስ።

ሌጀንድ ኢንተርናሽናል፤ ከአዲስ አበባ ውጭ በሁለት ክልሎች ላይ ስልጠና መጀመሩንና በ8 ክልሎች ፈቃድና ዕውቅና ማግኘቱንም ማስተር ሃይለየሱስ ፍስሃ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ ፌደሬሽን መስራች ግራንድ ማስተር ሔኖክ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ፤ እኛ ወደ ኢትዮጵያ የመጣነው አገራችን በማርሻል አርት ኮሪያና ጃፓን የደረሱበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ነው ብለዋል።

በ8 ክልሎች ፌደሬሽን መሥርተን እየሰራን ነው ያሉት ማስተር ሔኖክ፤ ዓላማቸው ሙያተኛው ትክክለኛ ሙያና ብቃት እንዲኖረው በማስተማር፣ የተሻለ አገር መገንባት መሆኑን ገልፀዋል።

ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ከተመሰረተ አንስቶ የተለያዩ ተግዳሮቶች እየገጠሙት መሆኑን ያልደበቁት መሥራቹ፤ “ተግዳሮቱን ተሸንፈን ነው የምናሸንፈው” ብለዋል።

የሌጀንድ ኢንተርናሽናል ዋና መ/ቤቶች በአሜሪካ፤ ጀርመንና ኮሪያ እንደሚገኙ የጠቀሱት ማስተር ሄኖክ፤ በዓለም ላይ ከሚሰሩ 7 ፌደሬሽኖችም ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታችን በፊት በ34 አገራት ውስጥ ነበር የምንሰራው ያሉት የሌጀንድ ኢንተርናሽናል መሥራች፤ አሁን ግን ወደ 56 አገራት አድርሰነዋል ሲሉም ተናግረዋል። በአፍሪካ ከ200ሺ በላይ ተከታዮች እንዳሏቸውም አውስተዋል።
84710cookie-checkየአዲስ አበባ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሶሴሽን 3ኛ ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና እየሰጠ ነው።የአዲስ …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE