አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ በ1 ቢሊዮን ብር የወላጅ አልባ ልጆች ማዕከል ልትገነባ ነው። አርቲስት መቅደስ ፀጋ…

Reading Time: < 1 minute
*
አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ በ1 ቢሊዮን ብር የወላጅ አልባ ልጆች ማዕከል ልትገነባ ነው።

አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ “መቅደስ የልጆች አድማስ” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ልታቋቁም እንደሆነ ዛሬ መጋቢት 12/2016 ዓም በካፒታል ሆቴል እና ስፓ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

ድርጅቱን ለማቋቋም ሃሳቡ የተፀነሰው ከ6 ዓመታት በፊት እንደሆነ አርቲስቷ ገልጻለች፣ ድርጅቱ በዋናነት ልዩ ትኩረት እና ጥበቃ ለሚያስፈልጋቸው ወላጅ አልባ ህፃናት ልጆች አስፈለጊውንና ሁሉን አቀፍ እንከብካቤ በመስጠት በቀጣይ የሕይወት ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንደሆነ የድርጅቱ የቦርድ አባል ደራሲ ውድነህ ክፍሌ ተናግሯል።

በማዕከሉ ውስጥ ለሚቆዩ ልጆች ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ከመስጠትና፣ የአካል ብቃት ማጎልመሻ ከማደራጀት ባሻገር፣ የማኅበራዊ ሕይወትና የአእምሮ ማበልፀጊያ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙሉ ጤንነታቸው የተረጋገጠ፣ በአካላዊ እድገታቸው የበቁ፣ በሥነ ልቦና፣ በግልና በማሕበራዊ ሕይወታቸው ጠንካራ የሆኑ እንዲሁም በአእምሮአዊ የተጠራ ችሎታቸው የተደነቁ እና በዕውቀት የዳበሩ ሆነው የመጪው ጊዜ ብሩህ እና ስኬታማ ዜጎችን እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

መቅደስ የልጆች አድማስ በማእከሉ የሚያድጉ ልጆች በሁሉም ረገድ ኢትዮጵያው እሴቶችን የተላበሱና አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ትኩረቱ እንደሆነ ተገልጿል።

ድርጅቱን ሙሉ ለሙሉ በመገንባትና በሙሉ አቅሙ ስራውን እንዲጀምር ለማድረግ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በሃያ አንድ ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ተቋም ነው::

FastMereja
84090cookie-checkአርቲስት መቅደስ ፀጋዬ በ1 ቢሊዮን ብር የወላጅ አልባ ልጆች ማዕከል ልትገነባ ነው። አርቲስት መቅደስ ፀጋ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE