“ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም!”
12 የሚሆኑ በዲውንሲንድረምና የአዕምሮ እድገት ውስንነት ዘርፍ ተሰማርተው ለልጆች ትምህርትና ሌሎች ስልጠናዎች እያደረጉ የሚገኙ ማኀበራት “በጋራ ድምጻችንን” እናሰማ በሚል ኀብረት የፈጠሩ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም የሚከበረውን የዲውንሲንድረም ዓመታዊ በዓል አስመልክተው ከኀብረቱ መካከል የተገኙት አምስት ማኀበራት ዓርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚሁ መርሀ ግብር ከተገኙት ማኀበራት መካከል አኔዱ የሆነው ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኀበር የትምህርት አገልግሎት የሰጣትና ማንበብ መጻፍ የቻለችው ብላቴና ቅድስት አበበ ዳውንሲንድረም ያለባቸውን ኢትዮጵያዊያን ወክላ ለማህበረሰቡ በንባብ ባስተላለፈችሁ መልዕክት ተከታዩን ስትል ተደምጣለች።
“ይህ ቀን በዓለም አቀፍ የዳውንሲንድረም ቀን ሲባል፣ በዓለም ለ13ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል” ብላ፣ ዋና ዓላማው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኝ የዳውን ሲንድረም ማኀበራት አንድ ላይ በመሰባሰብ ድምጻቸውን በጋራ የሚያሰሙበት መሆኑን አስረድታለች።
“ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ማኅበር ላለፉት 28 ዓመታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ለማህበረሰቡ ስለዳውን ሲንድረም ብሎም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ግንዛቤ እያስጨበጠ ቆይቷል” ብላለች።
“ዘንድሮ #ፍረጃ ይቁም! በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል” ያለችው ብላቴናዋ ቅድስት፣ ፍረጃ በአብዛኛው የተዛባ አመለካከት ዳውንሲንድረም ያለባቸውን ልጆች ሰዎች በዓይን እይታ የተዛባ በሆነ መንገድ “አይችሉም” የሚሉበት መንገድ መሆኑን አስረድታ፣ “ነገር ግን ሁላችንም የተለያዩ አቅሞችና ፍላጎቶች ያሉን ሰዎች ነን ስለዚህ ከመፈረጅ እንዲቆጠቡ” ስትል አሳስባለች።
“እኔና ጓደኞቼ መማር፣ መሰልጠን፣ መብታችን ተከብሮ ከሌሎች እኩል በልማት ሥራዎችን ተካፋይ ለመሆን የበኩላችንን ማድረግ እንችላለን። በዓሉ ግንዛቤ የምትጨብጡበት፣ የምትደሰቱበት እንዲሆንላችሀ አመኛለሁ። ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም!” በማለት አሳስባለች።
ሌላኛ ከኒያ ፋውንዴሽን የመጣው የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለበት ወጣት በበኩሉ፣ ባገኘው ስልጠና ሌሎች የአዕም እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች ለመርዳት ደረጃ እንደደረሰ ንግግር አድርጓል።
የዘርፉ ኃላፊዎች በበኩላቸው፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች “መማር አይችሉም፣ ቤተሰብ መመስረት አይችሉም” በሚል የሚሰነዘረው ፍረጃ ልጆቹ ወደ ኋላ እንዲቀሩ እያደረጋቸው መሆኑ ተነግሯል።
በዚህም አገልግሎት መስጫ ቦታ መኖሩን ካለማወቅና የፍረጃን ጉዳት ካለመገንዘብ አንጻር ብዙ ውስንነቱ ያለባቸውን ልጆች ወላጆቻቸው ቤት ዘግተው አስቀምጠዋቸው እንደሚገኙ፣ ነገር ግን ልጆቹ ወደ ማፈበራት ሂደው አገልግሎት ቢያገኙ እንደማንኛውም ሰው ሁሉን መድረግ እንደሚችሉ ማወቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።