በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የደንበኞች መጉላላትን ጨምሮ የደረሱ ጉዳቶች ስለመኖራቸው ተነገረ።
ጉዳቶችን በተመለከተ አስፈላጊዉን ምርመራ ተደርጎ ባንኩ ወደፊት ለህብረተሰቡ እንደሚያሳውቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ መጋቢት 7 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ስርዓት ላይ ያጋጠመውን ችግርና የአገልግሎት መቋረጥ በተመለከተ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
” ባንኮች በሥርዓቶቻቸዉ ላይ በየጊዜዉ የደህንነት ፍተሻ እንዲሁም የማሻሻያ ሥራዎችን ያከናዉናሉ ” ያለው ብሔራዊ ባንክ ፤ ” በሥርዓቶቹ ላይ በሚከናወን ለዉጦችና ፍተሻዎች የባንኮች አገልግሎት አልፎ አልፎ ሊቋረጥ ይችላል ” ብሏል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትናንትና ዕለት የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን አረጋግጫለሁ ሲል ገልጿል።
ችግሩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የባንኩን እና የደንበኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ እንደቆየና በተደረገው ርብርብ አገልግሎቶች እንዲመለሱ መደረጉን ጠቁሟል።
ብሔራዊ ባንክ በዚሁ መግለጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጋጠመው ችግር ጉዳቶች እንደደረሱበት ጠቁሟል።
ስለ ጉዳቶቹ በዝርዝር ያለው ነገር ባይኖርም አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ወደፊት ለህዝብ ይገለጻል ብሏል።
በተፈጠረው ችግር የተከሰቱ የደንበኞች መጉላላትን መከሰቱንም አመላክቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ተቋማት ላይ በየጊዜዉ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አመልክቶ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ያሉ በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙ የፋይናንስ ሥርዓቶች ደህንነቸዉ የተጠበቀ ነው ብሏል።