ጀንቦሮ ሪል ስቴት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ጋር ለመስራት ተስማማ።

“በጊዜ ግቡ” በማለት የሚታወቀው ጀንቦሮ ሪል ስቴት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ጋር ዛሬ ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል በደረሰው የጋራ ስምምነት መሠረት በተለያዩ ዓለማት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በልዩ ቅናሽ ቤት ለመሸጥ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል።

በስምምነቱም መሠረት ጀንቦሮ ሪል ስቴት ቦሌ ቡልቡላ 70 በመቶ ግንባታቸው የተጠናቀቁ አንድ መቶ ቤቶችን እንዲሁም ሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሦስት ዓመት ውስጥ ተገንብቶ በሚጠናቀቀው አፓርትመንት አራት መቶ ቤቶችን ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር አባላት በልዩ ቅናሽ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር በ2001 ዓ.ም የተቋቋመና በሥሩም ከ10,000 በላይ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ አባላት ያቀፈ ሲሆን ማኅበሩ ባለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ዳያስፖራው ከአገሩ ጋር በማገናኘት እንደ ድልድይ በመሆን በተጨማሪ ደግሞ ለዳያስፖራው ድምፅ የሆነና እየሆነም ያለ ማኅበር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማኅበሩ በተለያየ አቅጣጫ የዳያስፖራውን ጥቅም የሚያስጠብቁ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ ወደፊትም መሰል አጋርነቶችን በማጠናከር የአባላቶቹን ፍላጎት ለማርካት እየተጋ ይገኛል።

ጀንቦሮ ከገነባቸውና እየገነባ ካላቸው ስድስት ፕሮጀከቶች ሦስቱን ያስረከበ ሲሆን፣ በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ እያስገነባ ያለው ኪሩ አፓርታማ ከመኖሪያ ቤት በዘለለ ጥሩ የሕይወት ዘይቤና ቅንጡ አኗኗርን ለሚመኙ ኢትዮጵውያን የመጀመሪያው አማራጭ ነው፡፡ በ5,077 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ኪሩ ፕሮጀከት ሲጠናቀቅ፣ 30 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፣ ሰባት ወለል የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም አምስት ወለሎች ደግሞ ለዓለም አቀፍ ብራንድ ሱቆች በተጨማሪም 1,000 ካሬ ሜትር አረንጓዴ ስፍራ ይኖረዋል።

መነሻውን ቦሌ ቡልቡላ አድርጎ ከአራት ዓመታት በፊት በሪል ስቴት ዘርፍ ልማት ላይ የተሰማራው ጀንቦሮ ሪል ስቴት፣ በቦሌ ቡልቡላ አምስት ፕሮጀከቶችን እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለአካባቢው የተለየ ገፅታ የሚሰጠውን ኪሩ አፓርትመንት በመገንባት ላይ ይገኛል።

ፎቶ ተክሌ ማርኮን

62930cookie-checkጀንቦሮ ሪል ስቴት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ጋር ለመስራት ተስማማ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE