አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ «ሚዛን ትራክተር » ለማስተዋወቅ ብራንድ አምባሳደር ሆነ።

Reading Time: 2 minutes
ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ስራ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ባቋቋመው ዘመናዊ የማሽን ቴክኒዎሎጂ ዘርፍ ላይ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ተቋም ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ግብርናውን በማዘመን በኩል ከፍተኛ አስተዋፅአ እያበረከተ ይገኛል።

ትናንት ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ማምሻውን መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ጀርባ በሚገኘው ጭኮ ሬስቱራንት በተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ላይ እንደተገለጸው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ስራ ድርጅት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ግዙፍ ፋብሪካ የሚመረተውን « ሚዛን » በሚል ሀገረኛ ስያሜ የተሰጠው ትራክተር እንዲሁም ጄኔሬተር እና ፓምኘ ገቢያ ላይ ለማስተዋወቅ ለቀጣይ 12 ወራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የድርጅቱ ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ወልደ ገብርኤል ገልጸዋል።

አቶ ቴዎድሮስ አያይዘውም ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ስራ ድርጅት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከተመሠረተበት 2004 ጀምሮ በማሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው ፤ በዚህም በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ የሊፍት መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለስራ ዝግጁ ሲሆን በደብረ ብርሃን መስመር ላይ በሚገኘው ጫጫ ከተማ ደግሞ በስራ ላይ የሚገኘው ትራንስፈርመር ማምረቻ እና መጠገኛ ፋብሪካ በዋነኝነት የሚጠቀስ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።

ላለፉት አምስት አመታት በዘርፉ ጥናት የተደረገ ሲሆን
የኢትዮጵያ መልካምድርን ታሳቢ ተደርገው የሚገጠሙት ትራክተሮች ኢትዮጵያዊ ስያሜ ያላቸው ሲሆን ፤ የመለዋወጫ እቃዎች ግብአት ከነባለሙያው በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርሶ አደሩ በአካባቢው እንዲያገኝ እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል።

በፊልም ስራዎቹ እና በቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነው ሁሉገብ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ለቀጣዮቹ 12 ወራቶች ለመስራት ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ስራ ድርጅት መርጦኝ አብሮኝ ለመስራት ስለወሰነ ከልብ አመሰግናለሁ ሲል ምስጋናውን ለተቋሙ አቅርቧል።

አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በቀጣይ አንድ አመት ውስጥ የቴሌቪዥን ፣ የራዲዮ ፣ የማህበራዊ ትስስር ድረገጾች ፣ ፖስተሮችን ጨምሮ ለአርሶአደሩ የሚያስተዋውቅ ሲሆን ለአምባሳደር ሹመቱ የተከፈለውን ገንዘብ አርቲስቱ ከመናገር ተቆጥቧል።

ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ስራ ድርጅት ንጋት ኢንጂነሪንግ ትሬዲንግ ከተሰኘው እህት ኩባንያው ጋር በጥምረት በመሆን የሀገራችንን የውጭ ምንዛሪን በመቀነስ ፣ ቴክኖሎጂ በማስፋፋት እና ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

በቀጣይ አርብ ከግሎባል ኢትዮጵያ ባንክ ጋር በሚደረግ ስምምነት መሠረት አርሶ አደሩ በብድር የሚያገኘውን አዲሱ ትራክተር በቅርቡ ገቢያ ላይ ይውላል።

62440cookie-checkአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ «ሚዛን ትራክተር » ለማስተዋወቅ ብራንድ አምባሳደር ሆነ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE