«ገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል» የንግድ አውደ ርዕይ ተከፈተ።

Reading Time: < 1 minute

ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኢቨንትስ ያሰናዳው ከዛሬ ታህሳስ 6 ቀን እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ፤ ለ22ቀናት የሚቆየው 33ኛው «ገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል»
በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተከፈተ።

ከ500 በላይ የንግድ ተቋማት እና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎቢኚዎች የሚሳተፉበት የንግድ አውደ ርዕይ ላይ በየዕለቱ ዝነኛ አርቲስቶች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ የሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውግ ጀማነህ በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ ገልጸዋል።

ከ500 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ትልቁ የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሉታቸውን ለተጠቃሚው የሚቀርብ ሲሆን በገና ባዛር ላይ የቤት ዕቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ የህፃናትና የአዋቂ አልባሳት ፣ የስጦታ ዕቃዎች የተለያዩ ምርቶች የሚሸጡ ሲሆን በተጨማሪም ለበዓል የሚሆኑ የአስቤዛ ምርቶች ለሽማቹ በአምራች ዋጋ ያለገደብ ይቀርባሉ።

ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኤቨንትስ በ 1991 ዓ.ም የተቋቋመ የማስታወቂያና የፕሮሞሽን ድርጅት ሲሆን ተቋሙ የተመሠረተበትን 25ኛ የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል።

( ጌች ሐበሻ)
62420cookie-check«ገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል» የንግድ አውደ ርዕይ ተከፈተ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE